1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መንፈሳዊ የብልፅግና ሰባኪዎችን ማስቆም አስፈላጊ ይሆን?

02:39

This browser does not support the video element.

ሰኞ፣ ግንቦት 28 2015

ኬንያ ውስጥ በአጉል እምነት እራሳቸውን አስርበው የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ 200 አልፏል። የኬንያ ፖሊስ ባለፈው ሚያዚያ ምስራቃዊ ኬንያ የሚገኝ ሻካሆላ ደን ውስጥ በብዛት በጅምላ የተቀበሩ ሰዎች አግኝቷል።

የኬንያ ፖሊስ ባለፈው ሚያዚያ  ምስራቃዊ ኬንያ የሚገኝ ሻካሆላ ደን ውስጥ በብዛት በጅምላ የተቀበሩ ሰዎች አግኝቷል። ከዚያን ጊዜ አንስቶ የሟቾች ቁጥር ከፍ ብሎ 201 ደርሷል። ሟቾች ራሱን «ጉድ ኒውስ ኢንተርናሽናል ቸርች » ብሎ የሚጠራ ቡድን አባላት ሲሆኑ የአለም ፍፃሜ ከመምጣቱ በፊት ሰማይ ቤት ለመግባት በሚል ተርበው ሞተዋል። የኬንያ ባለስልጣናት ለዚህ የቡድኑ መሪ ፓውል ማኬንዚን ተጠያቂ ያደርጋሉ። 
ከዚህ ሞት ጋር ተያይዞ በመላው አፍሪቃ ያሉ የብልጽግና ሰባኪዎች በሌላው ህዝብ ዘንድ ጥያቄ ውስጥ ገብተዋል። እነዚህ ሰዎች ልዩ መንፈሳዊ ኃይል እንዳላቸው ሰዎችን እያሳመኑ በምትኩ ውለታ እንዲዋልላቸው ይጠይቃሉ። ነገር ግን ይህ በተከታዮቻቸው እና በቤተሰቦቻቸው ላይ አስከፊ መዘዝ ሊያስከትል ይችላል።  #77ከመቶው
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW