መክሊት መርሻና ፎቶግራፎቿ
ዓርብ፣ ግንቦት 17 2004ማስታወቂያ
ፎቶ ማንሳት የምንወድ? በዛሬው የወጣቶች ዓለም መክሊት መርሻ የተባለችውን ወጣት የጭውውት እንግዳችን እንድትሆን ዘንድ ጋብዘናታል። መክሊት ፎቶ ማንሳት ትወዳለች። ፎቶዎቿም ተወዳጅነት አግኝተው በቅርቡ በአንድ የጀርመን መፅሄት ላይ ይታተማሉ። «ከሰዎች ይልቅ ነፍሳትን ማንሳት ይቀለኛል» መክሊት መርሻ።
ቴክኖሎጂ በተሻሻለበት በአሁኑ ዘመን፣ የምናነሳቸውን ፎቶዎች በሰከንድ መልሰን መመልከት የምንችል ስለሆነ ፎቶ ማንሳት ከድሮ ጋ ሲነፃፀር ርካሽ እና ቀላል እየሆነ መቷል። ይሁንና ጥሩ ፎቶ አንሺ ለመሆን ከጥሩ ካሜራ ሌላ ጥሩ አመለካከት እና የግል ችሎታን ይጠይቃል። መክሊት በትርፍ ጊዜዋ ደስ የሚያሰኛትን የፎቶ ማንሳት የስራ ውጤቶች በአገር ውስጥ ለንግድ ለማዋል ጊዜ አልፈጀባትም።
የ 21 ዓመቷ መክሊት የአዲስ አበባ ነዋሪ ናት። ፎቶ ለማንሳት ስትል ወደ አዋሳ እና ሌሎች ከተሞችም ወጣ ማለት ታዘወትራለች። ስለ ፎቶ አነሳስ ስታወጋን« ከሰዎች ይልቅ ነፍሳትን ማንሳት ይቀለኛል» አለች። ለምን እንደሆነ አጫውታናለች። ሙሉ ጭውውቱን ከዘገባው ያድምጡ።
ልደት አበበ
ተክሌ የኋላ