1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መደራደር ለሚፈልጉ የታጠቁ ኃይሎች በሩ ክፍት ነው ፤ የአማራ ክልል መስተዳድር

ማክሰኞ፣ ጥር 21 2016

የአማራ ክልል መንግስት በክልሉ ከታጠቁ ኃይሎች ጋር ለድርድርና ለውይይት በሩ ክፍት መሆኑን አስታወቀ። በክልሉ አንፃራዊ ሰላም እየመጣ መሆኑንም አመልክቷል። በአንፃሩ በምስራቅ ጎጃምና በምዕራብ ጎጃም ዞኖች አንዳንድ አካባቢዎች ሰሞኑን ውጊያዎች እንደነበሩ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

 Desalegn Tasew -  Head, Peace and Security, Amhara Region
ምስል Alemenw Mekonnen/DW

የአማራ ክልል መስተዳድር ለታጣቂ ኃይሎች የመነጋገር በሩ ክፍት መሆኑ

This browser does not support the audio element.

የአማራ ክልል መንግስት በክልሉ ከታጠቁ ኃይሎች ጋር ለድርድርና ለውይይት በሩ ክፍት መሆኑን አስታወቀ። በክልሉ አንፃራዊ ሰላም እየመጣ መሆኑንም  አመልክቷል። በአንፃሩ በምስራቅ ጎጃምና በምዕራብ ጎጃም ዞኖች አንዳንድ አካባቢዎች ሰሞኑን ውጊያዎች እንደነበሩ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

የአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ዛሬ በጽ/ቤታቸው በሰጡት መግለጫ የክልሉ መንግስትም ሆነ የፌደራሉ መንግስት  ከማነኛውም ጥያቄ አለኝ ከሚል ኃይል ጋር  ልዩነቶችን በሰላምና በድርድር ለመፍታት ዝግጁ ነው ብለዋል፡፡

 “ፓርቲያችንና መንግስታችን፣ የማዕከላዊ ኮሚቴ ጭምር ስብሰባ አካሂዷል፣ ውሳኔዎች አስቀምጠዋል፣ በየትኛውም ጊዜና ሰዓት ቢሆን ሰላማዊ  በሆነ መንገድ ለመወያየት ሀሳብ አለኝ ብሎ ለመደራደር፣ ለውይይት የሚመጣ ማንኛውም ሰላምን የመረጠ ሁሉ፣ ትጥቅና ነፍጥ አንግቦ ከመንቀሳቀስ ውጪ ሰላማዊ ለሆነ ውይይት ለመምጣት ለሚፈልግ ሁሉ ዛሬም ነገም፣ የመንግስት የሰላም በር ክፍት ነው የሚል አቋም ላይ ተደርሷል፣ የክልልም፣ የፌደራልም አቋም ይህ ነው፡፡”

የአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ዛሬ በጽ/ቤታቸው በሰጡት መግለጫ የክልሉ መንግስትም ሆነ የፌደራሉ መንግስት  ከማነኛውም ጥያቄ አለኝ ከሚል ኃይል ጋር  ልዩነቶችን በሰላምና በድርድር ለመፍታት ዝግጁ ነው ብለዋል፡፡ምስል Awi zone communication office

የክልሉ የፀጥታ ሁኔታም የታሰበውን ያክል ባይሆንም እየተሻሻለ መምጣቱን ነው አቶ ደሳለኝ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ያስረዱት፡፡በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ የከፋዉ ግጭት

ኃላፊው ይህን ይበሉ እንጂ በተለያዩ አካባቢዎች አሁንም ህወትን የቀጠፉና ንብረት ያወደሙ ግጭቶች በአንዳንድ አካባቢዎች መኖራቸውን ነው አስተያየት ሰጪዎች የሚናገሩት፡፡

በምስራቅ ጎጃም ዞን የቢቸና ነዋሪ እንዳሉት ባለፈው ሳምንት በተለያዩ ቀናት በከተማዋ ሰላም ደፍርሶ ሰንብቷል፡፡

“አርብ ምሽት ላይ የተኩስ ልውውጥ ነበር፣ ተኩሱ እስከ ሶስት ሰዓት ዘለቀ፣ ተታኩሱ፣ የከተማዋ ከንቲባ ጽ/ቤትም ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ተቃጥሏል፣ ማእንዳቃጠለው ኤታወቅም፣ ትናንትና ምሽት 3 ሰዓት አካባቢ ደግሞ ቦምብ ፈንድቶ አንድ ሰው ቆስሏል አጠቃላይ ደስ የማይል ድባብ ነው በከተማው የሚታየው”

በተመሳሳይ ከባሕር ዳር ከተማ 35 ኪሎሜትር ያህል በምትርቀው መረዓዊ ከተማ ትናንት በነበረ ውጊያ  ሰዎች እንደሞቱና ንብረት እንደወደመ ስማቸው እንዳይጠቀስ፣  ድምፃቸውም እንዳይቀረፅ የፈለጉ የከተማዋ ነዋሪ አመልክተዋል፡፡ እንደዚሁም ትናንት በባሕር ዳር ከተማ ጊዮን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በፈነዳ ቦምብ የአንዲት መምህርት ህይወት ማለፉንና ዛሬ ቀብራቸው መፈፀሙን አንድ የአካባቢው ነዋሪ ነግረውናል፣ ለጥቃቱ ኃላፊነትን የወሰደ አካል የለም፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ አስተያየት እንዲሰጡኝ ለትምህርት ቤቱ ምክትል ርዕሰ መምህር  ብደውልና አጭር የፅሁፍ መልዕክት ብልክም ምላሽ ለመስጠት አልፈለጉም፡፡የአማራ ክልላዊ መንግስት የሰላም ጥሪዉን ማራዘሙ

በተመሳሳይ ከባሕር ዳር ከተማ 35 ኪሎሜትር ያህል በምትርቀው መረዓዊ ከተማ ትናንት በነበረ ውጊያ  ሰዎች እንደሞቱና ንብረት እንደወደመ ስማቸው እንዳይጠቀስ፣  ድምፃቸውም እንዳይቀረፅ የፈለጉ የከተማዋ ነዋሪ አመልክተዋል፡፡ምስል Alemnew Mekonnen/DW

በተለያዩ አካባቢዎች ውጊያዎችና ባለበት ሁኔታ በክልሉ ሰላም መጥቷል ማለት ይቻላል ወይ? ተብለው የተጠየቁት አቶ ደሳለኝ  በየቀኑ ትንኮሳ የሚያደርግ አካል የለም ማለት አይቻልም ነው ያሉት፣ የመንግስት የየፀጥታ ኃይል ሳስቶ በሚገኝበት ሁኔታ ጥቃቶች እንደሚደርሱ ተናግረዋል፡፡

በአማራ ክልል ከሐምሌ 2015 ዓ ም ጀምሮ በተቀሰቀሰው የሰላም መደፍረስ ምክንያት ክልሉ ሊጠናቀቅ ቀናት በቀሩት የስድስት ወራት  የአስቸኳ ጊዜ አዋጅ ስር ቆይቷል፡፡

ዓለምነው መኮንን

ታምራት ዲንሳ 

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW