መድኃኒት የተለማመደ ሳንባ ነቀርሳ በድሬዳዋ
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 26 2001ማስታወቂያ
በድሬዳዋ መስተዳድር መድኃኒት በተለማመደ ሳንባ ነቀርሳ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከቀድሞው አሁን መጨመሩን የመስተዳደሩ የጤና ቢሮ አስታውቋል ። የጤና ባለሞያዎች እንደሚያስረዱት ለዚህ ዓይነቱ የሳንባ ነቀርሳ የሚጋለጡት መድኃኒታቸውን የሚያቋርጡ የሳንባ ነቀርሳ ህሙማን ናቸው ። የተለየ መድኃኒት ለሚያስፈልጋቸው ለነዚህ ህሙማን ተገቢውን ህክምና ለመስጣት አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል ። ከችግሩ አሳሳቢነት የተነሳም ለጤና በለሞያዎች ስልጠና እየተሰጠ ነው ። ዮሀንስ ገብረ እግዚአብሄር ከድሬዳዋ ዝርዝር ዘገባ አለው ።
Yohannes G/Eegziabher, Hirut Melesse
Negash Mohammed