መጠነ ሰፊው እስር፤ የመንግስት ማብራሪያና የባለሞያ አስተያየት
ማክሰኞ፣ ግንቦት 16 2014ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንግስት ሰሞኑን «የሕግ የበላይነትን የማስከበር» ባለው ርምጃ በርካቶች ለእስር እየተዳረጉ ነው። የመንግሥትን ርምጃ የጅምላ እስር በሚል የሚተቹ በርካቶች ናቸው። የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ስለጉዳዩ ለዶይቼ ቬለ በሰጡት ማብራሪያ ሂደቱ በዋናነት ታጥቋል ያሉት ኢመደበኛ ቡድን እና ትስስር ያላቸው ያሏቸው አካላት ላይ ያነጣጠረ ነው ብለዋል። አስተያየት ሰጪዎች መንግስት አንድን ቡድን ዓልሞ ለመምታት ያቀደው ስልት ነው ሲሉም አስተያየታቸውን ሲሰጡ ይደመጣል። አንድ የሕግ ባለሞያ በፊናቸው መንግስት የሚወስዳቸው የትኛውም ርምጃዎች ውጤት የሚያመጡት ሕጋዊ ሂደታቸውን ከተከተሉ ብቻ ነው ብለዋል።
ሥዩም ጌቱ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሰ