1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

«ሙስሊሙን ኀብረተሰብ ከትምህርትና ሀገራዊ ተሳትፎ በማራቅ ዘላቂ ልማት አይኖርም»

ሰኞ፣ ኅዳር 15 2018

ሙስሊሙ ኀብረተሰብ ከሃይማኖቱና ከትምህርቱ አንዱን እንዲመርጥ እየተገደደ እንደሆነ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ገለፀ። «የኢትዮጵያ ሙስሊም ኀብረተሰብን ከሃይማኖቱ እና ከትምህርቱ አንዱን እንዲመርጥ በማስገደድ ከትምህርት እና ሀገራዊ ተሳትፎ በማራቅ የሚመጣ ዘላቂ ልማት አይኖርም» ሲል መግለጫ አውጥቷል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምስል፦ EIASC

«ሙስሊምን ኀብረተሰብ ከትምህርት እና ሀገራዊ ተሳትፎ በማራቅ ዘላቂ ልማት አይኖርም» የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት

This browser does not support the audio element.

«ሙስሊምን ኀብረተሰብ ከትምህርት እና ሀገራዊ ተሳትፎ በማራቅ ዘላቂ ልማት አይኖርም» የኢትዮጵያ  እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት 

 
ሙስሊሙ ኀብረተሰብ ከሃይማኖቱ እና ከትምህርቱ አንዱን እንዲመርጥ እየተገደደ እንደሆነ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ገለፀ። «የኢትዮጵያ ሙስሊም ኀብረተሰብን ከሃይማኖቱ እና ከትምህርቱ አንዱን እንዲመርጥ በማስገደድ ከትምህርት እና ሀገራዊ ተሳትፎ በማራቅ የሚመጣ ዘላቂ ልማት አይኖርም» ሲል የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ባለፈዉ ሳምንት መግለጫ አውጥቷል። ምክር ቤቱ ባወጣው መግለጫ እንደገለፀዉ የትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ የሙስሊም ተማሪዎችን ኢላማ ያረገ «ትንኮሳ» እና «የማሸማቀቅ» ያለዉ ተግባር እየፈፀመ ነው ሲል ገልጿል። ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸዉ ፤የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሼህ ሐሚድ ሙሳ «ትምህርት ሚኒስትሩ በአዳማ ከተማ በነበረዉ ስብሰባቸዉ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮችን አናግሬ በዚህ በዚህ መልኩ ካልሆነ በስተቀር፤ ተስፋ አጥተናል የሚል ነገር ስለተናገሩ እና ከዝያ ጋር ተያይዞ ያሉት በትምህርት ጉዳዮች በሁሉም ክልሎች የትምህርት ኃላፊዎች ሂጃብ እንዳይለበስ ሃይማኖታዊ ጫና በሚመስል መልኩ ተማሪዎችን እያንገላቱ መሆኑን ስለተገነዘብን መግለጫዉን ለማዉጣት ተገደናል» ብለዋል። ሼህ ሐሚድ ሙሳ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የተለያዩ ጫናዎችን ስናስተናግድ የኖርን ነን ሲሉም አክለዋል። የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ያወጣዉን መግለጫ ይዘን ም/ል ፕሬዚዳንት ሼህ አሊ ሙሳን አጠር ያለ ቃለ ምልልስ አድርገንላቸዋል። ቃለ ምልልሱን ተከትለን የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስትርን ለማግነጋገር ያደረግነዉ ጥረት ግን አልተሳካም። 

አዜብ ታደሰ 

ነጋሽ መሐመድ 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW