ሙስሊሞች በጀርመን ፣ ስደተኞች በግሪክ
ሐሙስ፣ ሰኔ 18 2001ማስታወቂያ
ሙስሊሞች በጀርመን
ጀርመን የሚኖሩ ሙስሊሞች ከዚህ ቀደም ከሚገመተው በላቀ ሁኔታ ከጀርመን ህብረተሰብ ጋር ተዋህደው እንደሚኖሩ አንድ የቅርብ ጊዜ ጥናት አስታወቀ ። በጥናቱ መሰረት በጀርመን ከሙስሊሞች ግማሽ ያህሉ የጀርመን ዜግነት የያዙ ሲሆን ከሴቶቹ ሰባ በመቶው ራሳቸውን አይከናነቡም ፤ ወይም ጉፍታ አያደርጉም ። በጥናቱ ጀርመን የሚኖረው ሙስሊም ብዛት ቀድሞ ከሚገመተው እጅግ ልቆ መገኘቱ አስገርሟል።
ስደተኞች በግሪክ
የበርካታ ስደተኞች መጉረፊያ ከሆኑት የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት አንዷ ግሪክ ናት ። የሚመጡብኝ ስደተኞች ከአቅሜ በላይ ሆነዋል ስትል የምታማርረው ግሪክ እጎአ እስከ 2009 መጨረሻ ድረስ ከቀድሞ ጠበቅ ያለ አዲስ የስደተኞች እና የተገን ጠያቂዎች ህግ ተግባራዊ ልታደርግ ነው ። ወደ ሌሎች የአውሮፓ ሀገራት መሸጋገሪያ የሆነችው ግሪክ ስደተኞችን በማሰቃየት ትወቀሳለች ።
ሂሩት መለሰ