1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ማብቂያ ያጣው የሱዳን ግጭትና ሰብዓዊው ቀውስ

ቅዳሜ፣ ኅዳር 29 2016

የሱዳን ጦር ኃይል ወደ 200 ሺህ የሚጠጋ ኃይል አለው። የፈጥኖ ደራሹ ኃይል ደግሞ ከ70 እስከ 100 ሺህ ይገመታል። የሱዳን ጦር ኃያል ታንኮች ሄሊኮፕተሮችና የአየር ኃይልን ጨምሮ በርካታ የጦር መሣሪያዎች አሉት። ያም ሆኖ ሁለቱም ተፋላሚዎች ተመሳሳይ ደረጃ ላይ እንደሆኑ ነው የሚነገረው። አንዳቸውም በሌላኛቸው ላይ የበላይነት መያዝ አልቻሉም።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት የUNITAMS ተልዕኮ እንዲቆም ሲወስን
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታ ምክር ቤት የUNITAMS ተልዕኮ እንዲቆም ሲወስን ምስል Eskinder Debebe/UN Photo/picture alliance

የተባባሰው የሱዳን ግጭትና ሰብዓዊው ቀውስ

This browser does not support the audio element.

ስምንት ወራት ባስቆጠረው የሱዳን ጦርነት የጦር ወንጀሎች፣ እልቂትና የጅምላ መፈናቀል መባባሱ እየተዘገበ ነው። የሀገሪቱን ሁኔታ የሚከታተሉ በርካታ ታዛቢዎች ሀገሪቱ ወይ ያልተሳካላት ሀገር ልትሆን ነው አለያም ወደ ሁለት የመከፈል ጫፍ ላይ ትገኛለች እያሉ ነው። ባለፈው አርብ የተመድ የጸጥታ ምክር ቤት በሱዳን የተቀናጀ ልዩ የሽግግር ድጋፍ ተልዕኮ በምህፃሩ UNITAMS ን ተልኮ ለማስቆም ተስማምቷል። ይህ የምክር ቤቱ ውሳኔ የሱዳን መንግሥት ጥያቄም ነበር። ሱዳን ይህን ያለችው ተልዕኮው የሚጠበቅበትን ማሳካት ተስኖታል በማለት ነበር።UNITMAS በወታደሩና በሲቭሉ ግፊት ሀገሪቱን ለረዥም ጊዜ የመሩት የኦማር አልበሽር አገዛዝ ካበቃ በኋላ ሱዳንን ወደዴሞክራሲ ለማሻገር በጎርጎሮሳዊው 2020የተመሰረተ ተልዕኮ ነበር። ይሁንና እንደታሰበው ሱዳን ወደ ዴሞክራሲ ከመሻገር ይልቅ እጣ ፈንታው ወደማይታወቅ ብጥብጥና ግጭት እየሄደች ይመስላል ይላል የዶቼቬለዋ የካትሪን ሼረር ዘገባ።

የተመ ድርጅቶች በመንግሥታት ፍላጎት ነው በየሀጋራቱ ስራቸውን የሚያካሂዱት ።ይሁንና በቅርብ ጊዜያት በተለይ በቅርቡ መፈንቅለ መንግሥት በተካሄደባቸው በማሊ እና በጋቦን ተመድ ብዙ ጥላቻ ገጥሞታል። ዩኒትማስ ከሱዳን ቢወጣም ሌሎች የመንግሥታቱ ድርጅት መስሪያ ቤቶች አሁንም ሱዳን ውስጥ ይሰራሉ።

የጦር ኃይሉና የፈጥኖ ደራሹ ኃይል አቅም

ሱዳን ውስጥ የሚዋጉት ሁለቱ ዋና ዋና ወታደራዊ ኃይሎች  የሱዳን ጦር ኃይል በእንግሊዘኛው ምህጻር SAF እንዲሁም ፈጥኖ ደራሹ ኃይል RSF ናቸው። በጀነራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሀን የሚመራው የሱዳን ጦር ኃይል ወደ 200 ሺህ የሚጠጋ ኃይል አለው። በአሀምዳን ዳግሎ ወይም በሌላ መጠሪያቸው ሄምደቲ የሚመራው የፈጥኖ ደራሹ ኃይል ደግሞ ከ70 እስከ 100 ሺህ ይገመታል። ይህ ኃይል የሚንቀሳቀሰው እንደ ደፈጣ ተዋጊ ነው።ግጭት በሱዳን ጦር ሠራዊትና ፈጥኖ ደራሽ ኃይል መካከልየመንግሥቱ ጦር ታንኮች ሄሊኮፕተሮች እና የአየር ኃይልን ጨምሮ በርካታ የጦር መሣሪያዎች አሉት። ከችሎታ አንጻር ግን ሁለቱም ወገኖች ተመሳሳይ ደረጃ ላይ እንደሆኑ ነው የሚነገረው። አንዳቸውም በሌላኛቸው ላይ የበላይነት መያዝ አልቻሉም። ሁለቱን ወገኖች ለማግባባት እንዲደራደሩም ለማድረግ ሙከራዎች ሲደረጉ ቆይተዋል። አሁንም እየተካሄዱ ነው።ሆኖም ሱዳን የሚካሄደው በትክክል ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ ግጭት ነው የሚሉት በጀርመኑ የዓለም አቀፍና አካባቢያዊ ጉዳዮች ጥናት ተቋም(ጊጋ)የሱዳን ጉዳዮች ተመራማሪ ሀገር አሊ ሁለቱን ተፋላሚ ወገኖች ማደራደሩም ቀላል አይደለም ይላሉ።
«የሚደራደሩበት መድረክ የሌላቸው እና አንገት ላንገት የተናነቁ ሁለት ወታደራዊ ድርጅቶች አሉ።ነገር ግን የሰላም ግንባታ እና ድርድርን በተመለከተ ለእነዚህ ኃይሎች የተለየ ስትራቴጂ የለም።»
የሲዳን ጦር ኃይልና ፈጥኖ ደራሹ ኃይል በእኩል ደረጃ ላይ የሚገኙበት ምክንያት አፈጣጠራቸው ነው ይላሉ የመስኩ ባለሞያዎች ።አምባገነን የሚባሉት የቀድሞው የሱዳን መሪ አልበሽር ናቸው በጎርጎሮሳዊው 2013 ፈጥኖ ደራሹን ኃይል ያቋቋሙት። ጦር ኃይሉ በጣም ተጠናክሮ አገዛዛቸውን የሚገዳደር መፈንቅለ መንግሥትም የሚያካሂድ እንዳይሆን ተብሎ ነው  የተቋቋመው። የፈጥኖ ደራሹ ኃይል ሌላው መነሻ ዳርፉር የሚገኘው የጃንጃዊድ ሚሊሽያ ነው። የተቋቋመውም ዳርፉር በሚገኙ የአረብ ጎሳዎች ነው።ዋና ዓላማቸውም ከዳርፉር አረብ ያልሆኑ ሰዎችን የጥቃት ዒላማ ማድረግ ነው። ይህ አሁንም ቀጥሏል።  

ዛቦት በተባለው የስደተኖች መጠለያ የሚገኙ የሱዳን ተፈናቃዮችምስል Marie-Helena Laurent/WFP/AP/picture alliance

 ለወራት የተካሄደው ግጭት 

ከአል በሽር ውድቀት በኋላ ወታደሩ ምርጫ እስኪካሄድ ድረስ ከሲቪሉ ጋር ስልጣን ለመጋራት ተስማማ። ምርጫውም በጎርጎሮሳዊው ነሐሴ 2019 እንዲሆን ቀጠሮ ተያዘ። አሳሳቢዉ የሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነትይህ ሳይሳካም በጎርጎሮሳዎው 2021 መጨረሻ የሱዳን ጦር ኃይል መፈንቅለ መንግሥት በማካሄድ ወደ ዴሞክራሲ የሚደረገው ሽግግር ቆመ።ያም ሆኖ የሲቪል ፓርቲዎችን ጨምሮ  ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉ እንዴት ስልጣን እንደሚጋሩ አስቸጋሪ የነበሩ ቢሆንምድርድሮች ሲካሄዱ ቆዩ ።ሁለቱ ወታደራዊ ኃይሎች ግን የሱዳን ሲቪልማኅበረሰብን ከብሔራዊው ፖለቲካ ማስወገድ ቻሉ ብለዋል አሊ። በመጋቢት ወር ,ጥኖ ደራሹ ኃይል በሱዳን ጦር ኃይል ስር እንዲሆን የቀረበው ሀሳብ ውጥረቱን አባባሰው። ሱዳንን ወደ ዴሞክራሲያዊ ሽግግር ለመውሰድ የተደረሰበት ስምምነት በጎርጎሮሳዊው 2022 ማብቂያ ላይ ተፈረመ። የሱዳን ጦር ኃይልንና ፈጥኖ ደራሹን ኃይል ጨምሮ ከ40በላይ የሲቪል ቡድኖች የዚህ ስምምነት ተካፋይ ነበሩ።ስምምነቱ በሚያዚያ አጋማሽ ላይ እንዲጠናቀቅ ታስቦ እያለ በዚያው በሚያዚያ በጦር ኃይሉና በፈጥኖ ደራሹ ኃይል መካከል ውጊያ ተጀመረ ።  

የሱዳን ሰብዓዊ ቀውስ


የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ፈጥኖ ደራሹ ኃይል እንደ ቀድሞው ሁሉ አረብ ያልሆኑ ሰዎች ላይ ባነጣጠረበት ጥቃት ከህዳር መጀመሪያ አንስቶ አሰቃቂ ግድያዎችን አስገድዶ መድፈርና ዝርፍያ መፈጸሙን በሕይወት የተረፉ እንደነገሯቸው መዝግበዋል።ቅርጽና አድማሱን ያሰፋው የሱዳን ጦርነት በፈጥኖ ደራሹ ኃይል ጥቃት በ2023 መጀመሪያ ላይ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ የማሳሊት ጎሳ አባላት ከመኖሪያቸው ተሰደዋል።በህዳር የተገደሉት ቁጥር ከ800 እስከ 2 ሺህ ይገመታል። በርካቶችን ወደ ጎረቤት ቻድ ተሰደዋል።በአሁኑ ጊዜ ግማሽ ሚሊዮን የሱዳን ስደተኞች ቻድ ውስጥ ይገኛሉ። በሱዳን የኖርዌይ የስደተኞች ምክርቤት ተጠሪ ዊልካርተር የሱዳኑ ጦርነት ያስከተለው ሰብዓዊ ቀውስ የሚስተካከል የለም ይላሉ ።

የወሲብ ጥቃት ሰለባ የሆነች 15 ዓመት ሴት ልጅ በኤልገኔይና ምዕራብ ዳርፉርምስል Zohra Bensemra/REUTERS


«ይህ ቢያንስ በክፍለ ዓለሙ በዓለምም ደረጃ ቢሆን ትልቁ የመፈናቀል ቀውስ ሆኗል። ጨለምተኛ ሁኔታ ነው። እውነት ለመናገር በሚቀጥለው ዓመት እንደሚብስ ነው የምንጠብቀው።ረሀብ የማይቀርነው። እጅግ አስከፊ አረመኔያዊ ድርጊቶች ተፈጽመዋል።እነዚህን ለማስቀረት የተሰራው በጣም ጥቂት ነው።እየፈረሰች ያለች ሀገር፤  የጤና አጠባበቅ የትምሕርት ስርዓት ምናልባትም መሰረታዊ ባንኮች መቀጠላቸው ያጠራጥራል።የገንዘብ እርዳታዎች ዝቅተኛ ናቸው። ማስፈጸም አቅምም እንዲሁ።»በአሁኑ ጊዜ በሱዳን ሰብዓዊ ሁኔታው ተባብሷል።ከዚህ ቀደም15.8 ሚሊዮን የተገመተው እርዳታ ጠባቂ ቁጥር አሁን 25 ሚሊዮን ተጠግቷል። አንዳንድ ታዛቢዎች የአሁኑ ግጭት ሱዳንን ለሁለት ሊከፍላት ይችላል ይላሉ። ሌሎች ደግሞ ውጊያው መፍትሄ ላያገኝ ባይ ናቸው። 

ካትሪን ሼረር

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW