1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ማኅበረሰቡን የፈተነዉ የኑሮ ዉድነት

ሰኞ፣ የካቲት 8 2013

በኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት ያስከተለው ከፍተኛ የኑሮ ውድነት የከተሜውን ሕይወት እየፈተነው ይገኛል። መንግሥት አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ እያደረገ ቢሆንም መቋሚያ ያጣው የሸቀጦች የዋጋ ማሻቀብ ከሥራ አጥነት ፣ ከወጪ ንግድ መቀዛቀዝ፣ ከውጪ ምንዛሪ እጥረት ፣ ከብር የመግዛት አቅም መዳከም ጋር ተደማምሮ አናኗርን ፈተና ውስጥ እየጣለው ይገኛል።

Äthiopien | Traditioneller Markt in Debre Markos
ምስል DW/E. Bekele

ከብር የመግዛት አቅም መዳከም ጋር ተደማምሮ ፈተና ሆዋል

This browser does not support the audio element.


በኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት ያስከተለው ከፍተኛ የኑሮ ውድነት የከተሜውን ሕይወት እየፈተነው ይገኛል። መንግሥት አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ እያደረገ ቢሆንም መቋሚያ ያጣው የሸቀጦች የዋጋ ማሻቀብ ከሥራ አጥነት ፣ ከወጪ ንግድ መቀዛቀዝ፣ ከውጪ ምንዛሪ እጥረት ፣ ከብር የመግዛት አቅም መዳከም ጋር ተደማምሮ አናኗርን ፈተና ውስጥ እየጣለው ይገኛል። የምጣኔ ኃብት ባለሙያዎች በተለይ ሰሞነኛው የነዳጅ ዋጋ ክለሳ ያስከተለው የዋጋ ጭማሪ ሌላ ራስ ምታት መደቀኑን አበክረው እየተናገሩ ሲሆን መንግስት በበኩሉ ስለዚህ ጉዳይ ያለው ነገር የለም። ኢትዮጵያ የገባችበት የፖለቲካ ምስቅልቅል ለኑሮ ውድነት መባባሱ ተጨማሪ ችግር መሆኑም እዚህም እዚያም ይደመጣል።


ሰለሞን ሙጬ  

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW