1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

"ማንንም የማጥቃት ፍላጎት የለንም" - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ሐሙስ፣ ኅዳር 17 2019

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ "ማንንም የማጥቃት ፍላጎት የለንም" ሲሉ ከኤርትራ ጋር በተገናኘ ከሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጡ። የኢትዮጵያ መከላከያ መጠንከሩ ለጎረቤት አገራት ሥጋት አይደለም ያሉት ጠ/ትሩ ግን "ማንም ሰው ወደ ኢትዮጵያ ድንበር መጥቶ ኢትዮጵያን ወርሮ በክብር መመለስ አይችልም" ሲሉ በብርቱ አስጠንቅቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ እአአ - 26.11.2026
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ እአአ - 26.11.2026ምስል፦ Ethiopian House of Peoples' Representatives

"ማንንም የማጥቃት ፍላጎት የለንም" - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

This browser does not support the audio element.

"ማንንም የማጥቃት ፍላጎት የለንም" - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ "ማንንም የማጥቃት ፍላጎት የለንም" ሲሉ ከኤርትራ ጋር በተገናኘ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጡ። የኢትዮጵያ መከላከያ መጠንከሩ ለጎረቤት አገራት ሥጋት አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያም ሆኖ ግን "ማንም ሰው ወደ ኢትዮጵያ ድንበር መጥቶ ኢትዮጵያን ወርሮ በክብር መመለስ አይችልም" ሲሉ በብርቱ አስጠንቅቀዋል። መንግሥታቸው ዉግያ እንደማያስፈልገው ለሕዝብ እንደራሴዎች ያረጋገጡት ዐቢይ "ዉግያ ካለ ግን ኢትዮጵያ አሸናፊ" እንደምትሆንም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉና ከመንግሥት የሚዋጉ የትጥቅ ኃይሎች የሌሎች "መሣሪያ" ከመሆን ወጥተው ወደ መተባበር እንዲገቡም ጥሪ አድርገዋል። ሆኖም መንግሥታቸው በቅርቡ ይወድቃል በሚል የሚነሳን ሀሳብ እንዳለ ገልፀው ይህ ግን ትክክል እንዳልሆነ ጠቅሰዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሎ ከምክር ቤት አባላት ከቀረቡላቸው ጥያቄዎች መካከል መንግሥትን "ኢትዮጵያን የማፈራረስ የግብፅን ተልዕኮ ተቀብለው ኢትዮጵያን የሚወጉ እና ሉዓላዊነቷ ላይ አደጋ የሚደቅኑ" የተባሉ ኃይላት በአገር ክህደት ወንጀል የሚያስጠይቅ ቋሚ የሕግ ማዕቀፍ እንዲኖር የሚጠይቀው ይገኝበታል። ለዚህ በሰጡት ምላሽ ታጣቂዎች ምንም ቢያደርጉ በያዙት መንገድ መቼም እንደማይሳካላቸው ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ  በኢትዮጵያ አሳሳቢ የሰላምና ደኅንነት ችግሮች መንሰራፋታቸው ተጠቅሶ የመንግሥታቸውን ምላሽ ተጠይቀዋል። በሀገሪቱ እየተፈጸሙ ያሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች "እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ" ስለመድረሳቸው፣ የንፁሃን ዜጎች ግድያ፣ የንብረት ዘረፋ፣ ከበባ፣ መንገድ መዝጋትና የዜጎች ሞት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱም ተገልፆ ይህንን ለምን ማስቆም እንዳልተቻለ ተጠይቀዋል። ተደጋጋሚ የጅምላ ግድያ በሚፈፀምበት አርሲ "የመንግሥት መዋቅር ቢፈተሽ" ተብሎም ጥቆማ ቀርቦላቸዋል።

የኢትዮጵያ ፓርላማ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ እአአ - 26.11.2026ምስል፦ Ethiopian House of Peoples' Representatives

በሀገሪቱ "የፀጥታ ችግር" መኖሩን ያመኑት  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ  ሆኖም ከፍተኛ መሻሻል መኖሩንና ደረጃ በደረጃ የሚፈታ መሆኑን ገልፀዋል። መንግሥት የኤርትራን "ተደጋጋሚ" የተባለ አፍራሽ ተግባር እስከመቼ ይታገሳል የሚል ጥያቄም ተነስቶ ነበር። "ሰሜን ዕዝ ሲጠቃ ወታደር ወደ ኤርትራ ሲያፈገፍግ ያሳዩይ የመልካም ጉርብትና ባሕሪ ይመሰገናል"

ኢትዮጵያን ባነሳችው ከቀይ ባሕር የመጠቀም ፍላጎት መነሻ የባሕሩ ተዋሳኝ ሀገራት ሀገሪቱን በምድርም በሰማይም የመዝጋት ሀሳብ እንዳላቸውም ገልፀዋል። የኤርትራ መንግሥት አንድም የኢትዮጵያን ጠላት ከማስታጠቅና፣ ማስታጠቂያ መስመር ከመሆን እና ለኢትዮጵያ ጠላቶች መተባበር እንዲያቆም እንፈልጋለን ያሉት ጠቅላይ ሚኑስትሩ፣ በሌላ በኩል ለጋራ ልማት አብረን እንሥራ የሚል ጥሪ አድርገዋል። ከዚህ ያለፈውን ግን መንግሥታቸው እንደማይቀበል አረጋግጠዋል። "ማንም ሰው ወደ ኢትዮጵያ ድንበር መጥቶ ኢትዮጵያን ወርሮ በክብር መመለስ አይችልም።" 

የሀገራዊ ምክክርን ውጤት አተገባበርን በተመለከተ የተጠየቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ መንግሥት "እያንዳንዱ ሐሳብ መተግበር አለበት የሚል አቋም" እንዳለውና ለዚህም ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል። ለረጅም ጊዜ ሊሠሩ ያልቻሉት የሕዝብና ቤት ቆጠራ እንዲሁም የአካባቢ ምርጫ በቅርብ ጊዜ እንደማይከናወኑም ከምክር ቤት አባል ለተነሳ ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

ሰለሞን ሙጬ 

አዜብ ታደሰ 

ነጋሽ መሐመድ

Edited by: Negash Mohammed ነጋሽ መሐመድ
ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW