1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ማንኮራፋት የጤና እክል ነዉን?

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 22 2010

ማንኮራፋትን የካምብሪጅ መዝገበ ቃላት 'በመኝታ ጊዜ የሚፈጠር እጅግ የሚረብሽ ድምፅ' ሲል ይተረጉመዋል። ማንኮራፋት በማንኛውም ዕድሜና ፆታ ክልል ውስጥ ሊፈጠር የሚችል ነው።

Professor Johan Verbraecken von Uniklinik Antwerpen
ምስል፦ DW/D. Sisay

ማንኮራፋት የጤና እክል ነዉን?

This browser does not support the audio element.

በተለይም ግን በወፍራም ሰዎች፣ በአልኮል ጠጪዎችና ሌሎች ተዛማች መደበኛ ጤናን ሊያውኩ የሚችሉ ልማዶችን በሚያዘወትሩ ሰዎች ላይ ሊከሰት ይችላል። የመኝታና ትራስ አለመመቸትም ሌላኛው ምክንያት ነው። አልፎ አልፎ የማንኮራፋት ድምፅ ማሰማት ብዙም የጤና እክል ባይፈጥርም አብሮ በሚተኛ ሰው ላይ ግን ተፅዕኖ መፍጠሩ እንደማይቀር የጤና መዛባትን እየተከታተለ ጥናትና የመፍትሔ ሀሳብ የሚያቀርበው ዌብ ኤም.ዲ. የተባለው ድረ ገፅ ያብራራል። 
የሚያንኮራፋ ሰው በራሱ እና አብሮ በሚተኛው የአልጋ ተጋሪ ላይ የእንቅልፍ ጥራትን መቀነስ ብቻ ሳይሆን የእንቅልፍ መዛባትን ጭምር ያስከትላል።  በቤልጅየም የአንትወርፐ ዩኒቨርስቲ ሆስፒታል የእንቅልፍና ተዛማጅ ጉዳዮች ዶክተር የሆኑት ፕሮፌሰር ዮሃን ቨርብራከን እንዳሉት፣ "ማንኮራፋትን እንደ ቀላል ነገር የሚያዩት ብዙ ሰዎች ናቸው። በተገቢው መንገድ ወደ ህክምና መስጫ ተቋማት ሔዶ ተገቢውን ህክምና ማግኘት ካልተቻለ መዘዙና ውጤቱ ግን የከፋ ሊሆን ይችላል።

ምስል፦ picture-alliance/BSIP/Chassenet

ዳግማዊ ሲሳይ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW