1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክና የተመድ ሰላም አስከባሪዎች

ረቡዕ፣ የካቲት 2 2008

ማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ የሚገኘው የተመ ሰላም አስከባሪ ኃይል ወታደሮች ጥቂት ከመሆናቸው በተጨማሪ ብቃት የሚጎላቸውና የመሣሪያ እጥረት ያለባቸው መሆኑን አምነስቲ አስታውቋል።

UN Soldaten in Bangui
ምስል፦ picture-alliance/AA

[No title]

This browser does not support the audio element.


ማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ሰላም አስከባሪ ኃይል እንዲጠናከር ጥሪ ቀረበ። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ትናንት ባወጣው ዘገባ በሀገሪቱ የተሰማራው የተመ ሰላም አስከባሪ ኃይል ወታደሮች ጥቂት ከመሆናቸው በተጨማሪ ብቃት የሚጎላቸውና የመሣሪያ እጥረት ያለባቸው መሆኑን አስታውቋል። የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምዕራብ እና መካከለኛ አፍሪቃ ክፍል ምክትል ሃላፊ ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት ሰላም ለማስከበር የተሰማራው የተመድ ኃይል ባለፈው መስከረም በሀገሪቱ የተከሰተውን ግጭት ለማብረድ ፈጥኖ ባለመንቀሳቀሱ ከ70 በላይ ሰዎች ሲገደሉ በሺህዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል። የዶቼ ቬለዋ ጄን አይኮ ኬሜዝ የፃፈችዉን የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል እንደሚከተለዉ አዘጋጅቷል።


ጄን አይኮ ኬሜዝ /ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW