1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ሜዲቴራንያን ላይ የወደቀው የኢትዮጵያ አውሮፕላን

ሰኞ፣ ጥር 17 2002

ትናንት ከለሊቱ ስምንት ሰዓት ተኩል ከሊባኖስ ዋና ከተማ ከቤይሩት አውሮፕላን ማረፊያ እንደተነሳ አየር ላይ ተበታትኖ ሜዲቴራንያን ባህር ላይ የወደቀው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አደጋ መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 737-800 አውሮፕላንምስል፦ AP

የአየር መንገዱ ስራ አስኪያጅ አቶ ግርማ ዋቄ ዛሬ እንደተናገሩት አስራ አራት አባላት የሚገኙበት የአየር መንገዱ አጣሪ ቡድን ወደ ቤይሩት ሄዷል ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንደሚለው ትናንት ለሊት የተከሰከሰው ቦይንግ 730-800 አውሮፕላን አየር መንገዱ ኤሮ ስፔስ ከተባለው ድርጅት ተከራይቶ የሚገለገልበት አውሮፕላን ነው ።

መርከቦች በፍለጋ ላይምስል፦ AP

አደጋ የደረሰበት የኢትዮጵያዉ አዉሮፕላን ለገጠመዉ ችግር ምክንያት የሆነዉ ምንድ ነዉ የሚለዉ እስካሁን እየተጣራ ያለ ጉዳይ ነዉ። አደጋዉ ከሽብር ጋ ግንኙነት እንደሌለዉ ከልባኖስና ኢትዮጵያ መንግስታት ተነግሯል። አዉሮፕላኑ አየር ሆኖ ለአራት ተከፋፍሎ ባህር ላይ መከስከሱ ነዉ የሚገለጸዉ።ከአፍሪቃ አየር መንገደች አዳዲስ አውሮፕላኖችን በመግዛት እና ወደ ሀምሳ ስድስት አገራት በመብረር በአንጋፋነቱ የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓለም ከፍተኛ ተወዳዳሪዎች ከሚባሉት አየር መንገዶች ተርታ ይሰለፋል ።

ከባህር ውስጥ የተለቀሙ ዕቃዎችምስል፦ AP

በትርፋማነቱ የሚታወቀው ይኽው አየር መንገድ በበራ ዋስትናው ዝና ካተረፉ አየር መንገዶች ጋር ይጠቀሳል ። አየር መንገዱ በእስከዛሬ ታሪኩ የአሁኑን ሳይጨምር እ.ጎ.አ ከ 1980 በኃላ ሁለት አሰቃቂ የአውሮፕላን አደጋዎች ናቸው የደረሱበት ።

ታደሰ ዕንግዳው ከአዲስ አበባ የወጡ መግለጫዎችን ተከታትሏል

ሸዋ ለገሰ ወደቤይሩት ደዉላ ዘገባ አጠናቅራለች።

ጌታቸው ተድላ የአየር መንገዱን የአደጋ ታሪክ ተመልክቷል

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW