1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሜጀር ጀነራል ክንፈ ተያዙ

ማክሰኞ፣ ኅዳር 4 2011

በቁጥጥር ስር የዋሉት የቀድሞ የኢትዮጵያ የብረታ ብረት እና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዳይሬክተር ሜጄር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ከተያዙበት ቦታ ወደ አዲስ አበባ ተወሰዱ። ሜጄር ጀነራል ክንፈ በ 48 ሰዓታት ዉስጥ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Police have detained Major General Kinfe Dagnew, former Director General of the state-owned Metals and Engineering Corporation
ምስል Ethiopian government communication

በቁጥጥር ስር የዋሉት የቀድሞ የኢትዮጵያ የብረታ ብረት እና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዳይሬክተር ሜጄር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ከተያዙበት ቦታ ወደ አዲስ አበባ ተወሰዱ። በሄሌኮፕተር አዲስ አበባ አየር ማረፍያ ሲደርሱ እጃቸዉ በካቴና ታስሮ በፀጥታ አስከባሪዎች ታጅበዉ አንድ ፒካፕ መኪና ሲገቡ ታይተዋል። ከኮርፖሬሽኑ ሥራ ጋር በተያያዘ በከባድ የሙስና ወንጀል የሚጠረጠሩት  ጀነራል ክንፈ በምዕራባዊ ትግራይ በኩል ባታር በተሰኘው አካባቢ ፤ አካባቢዉ ላይ የሚገኙ የማኅበረሰቡ አባላት እና በመከላከያ ኃይል ትብብር መያዛቸዉ ተመልክቶአል። ሜጄር ጀነራል ክንፈ በ 48 ሰዓታት ዉስጥ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ፣በሙስና  ወንጀል ተጠርጥረው የተያዙ  የ27 ባለሥልጣናት ስም ዝርዝርን ዛሬ ይፋ አድርጓል። ከተያዙት ባለስልጣናት መካከል  ብርጋዴር ጀነራል ጠና ቁርንዴ ኢጄታ፣ በብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ)ምክትል ዋና ዳይሬክተር፤ የማርኬቲንግ ሃላፊ ፣ብርጋድየር ጀነራል ብርሃ በየነ፤ በብረታ ብረት ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን የኮርፖሬት ኦዲት እና ኢንስፔክሺን ኃላፊ፤ብርጋድየር ጀነራል ጥጋቡ ፈትላ መረሳ፣ በብረታ ብረት ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የኮርፖሬት ሎጂስቲክስ እና ሰፕላይ ኃላፊ እንዲሁም ብርጋድየር ጀነራል ሃድጉ ገብረ ጊዮርጊስ ገብረ ሥላሴ በብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የኮርፖርት ኒው ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ሃላፊ ይገኙበታል።

ምስል picture-alliance/U.Baumgarten

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ 

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW