1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ምላሽ ያላገኘው የታጋች ተማሪዎች ጉዳይ

ሰኞ፣ የካቲት 30 2012

አሁንም ስለልጆቻቸው ተጨባጭ መረጃ እንዳላገኙ ከደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲጓዙ የታገቱ ተማሪዎች ወላጆች ገለፁ። የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጉዳዩን በቅርበትና በትኩረት እየተከታተልኩት ነው ብሏል። ከወራት በፊት ባልታወቁ ሰዎች ታገቱ የተባሉ ተማሪዎች ጉዳይ አሁንም ምላሽ ያላገኘ እንቆቅልሽ ሆኖ እንደቀጠለ ነዉ።

Äthiopien | Proteset | Entführte Studenten
ምስል privat

መንግሥት ስለልጆቻችን መረጃ ይሰጠናል ብለን እየጠበቅን ነዉ

This browser does not support the audio element.


አሁንም ስለልጆቻቸው ተጨባጭ መረጃ እንዳላገኙ ከደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲጓዙ የታገቱ ተማሪዎች ወላጆች ገለፁ። የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጉዳዩን በቅርበትና በትኩረት እየተከታተልኩት ነው ብሏል። ከወራት በፊት ከደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ወደ ቤተሰቦቻቸው ጋር እያመሩ ሳለ መንገድ ላይ ባልታወቁ ሰዎች ታገቱ የተባሉ ተማሪዎች ጉዳይ አሁንም ምላሽ ያላገኘ እንቆቅልሽ ሆኖ እንደቀጠለ ነዉ። ጉዳዩ ከቤተሰብ አልፎ በአማራ ክልል በአብዛኛዎቹ ከተሞች ታላላቅ ሰላማዊ ሰልፎች እንዲካሄዱም ምክንያት ሆኗል። ያም ሆኖ እስካሁን ተማሪዎቹን የተመለከተ ምንም የተጨበጠ ነገር እንደሌለ ነው የታጋች ተማሪዎች ቤተሰቦች የሚናገሩት። ከታጋች ተማሪዎች ወላጆቸ መካከል በማእከላዊ ጎንደር ዞን ምዕራብ ደንቢያ ወረዳ የጯሂት ከተማ አካባቢ ነዋሪው መርጌታ የኔነህ አዱኛ ከመንግስትም ሆነ ከሌላ አካል ያገኘነው ነገር ባለመኖሩ ለፈጣሪ ትተናል ብለዋል፡፡የተፈጠረው አጋጣሚ ሌሎች ልጆችን ለማስተማር ተስፋ አንዳስቆጠራቸው፣ ልጆችም ትምህርት ቤት ለመሄድ ድፍረትን እንዳጡና በህብረተሰቡ ዘንድም ተማሳሳይ ማሕበራዊ ተፅዕኖ መፍጠሩን መሪጌታ የኔነህ ተናግረዋል። በምዕራብ ጎጃም ዞን ወንበርማ ወረዳ የሚገኙትና የአንዲት ታጋች ተማሪ ወንድም የሆኑት ዲያቆን በልስቲ አያል በበኩላቸው መንገግስት ያለውን እውነታ ቢያሳውቅ ተገቢ መሆኑን አመልክተው የእህታቸው አለመገኘት በቤተሰብ አባላት ላይ የጤና ጉዳት እያስከተለ መሆኑን ተናግረዋል፡፡የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብርኃም አለኸኝ ሰሞኑን በክልሉ ሲሰጥ የቆየውን የከፍተኛና መካከለኛ አመራር ማጠናቀቅን በመስመልከት በጽ/ ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ስለታገት ተማሪዎች ጉዳይ በተለይ ከዶቼ ቬለ ለቀረበላቸው  ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ጉዳዩ ያልተዘነጋና ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ ነው ብለዋል። 

ዓለምነው መኮንን


አዜብ ታደሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ  
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW