1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ምልኪ በጉጂ ብሄረሰብ

ሰኞ፣ ጥቅምት 18 2000

በአገራችን በተለያዩ ብሄረሰቦች ባሉ አገረሰባዊ እምነት ለምሳሌ በህልም ጥርስ ሲወልቅ እገሌ ይሞታል፣ ማለዳ ከቤት ሲወጣ ቁርስ ቀምሶ መዉጣት፣ በቤተሰበብ ተመርቆ ትፍትፍ ተሰኝቶበት መንገድ መጀመር ቀኑ ሲቀና ይዉላል የሚል እምነት አለ

ምስል AP

ከቤት ከመዉጣት በፊት በቤቱ ገዳም የሆነ ሰዉ እጅ ካስታጠበ ይቀናል የሚል እምነትም አለ። በሌላ በኩል ከመጥፎ ነገር ጋር የተያያዙ ትንቢቶችን ስንመለከት መንገድ ሲጀመር እንቅፋት ብጤ ካጋጠመ አይቀናም ባዶ እንስራ ያዘለች ሴት መንገድህን ከአቋራጠች አይቀናም፣ ባዶ አቆማዳ የተጫነች አህያ መንገድ ላይ ስታጋጥም አይቀናም የሚሉ የተለያዩ እምነቶች አሉ። በጉጂ ብሄረሰብ ዘንድ የሚታየዉ ምልኪ ምን ይመስላል? የጉጂ ብሄረሰብ በኦሮሞያ ክልላዊ መንግስት በጉጂ እና በበቦረና ዞኖች፣ በተለይ ቡሌ ሆራ ገላና አባያ ቦሪ አዶላ ግርጃ ዋደራ ኦዶ ሻኪሶ ዳማ ተልታሌ ሊበን እና አሪሮ ወረዳዎች ዉስጥ ይገኛል። ለዩንቨርስቲ ትምህርት ምረቃ ስራቸዉ በጎጂ ኦሮሞ ዘንድ ያለዉን የምልኪ አይነት በጥናታቸዉ ያፈሩት አቶ ደቻሻ ሰርቤሳ በማህበረሰቡ ካጋጠሙዋቸዉ ምልኪዎች ይገልጹልናል መልካም ቆይታ።

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW