ምርጫና ጥላቻ
ዓርብ፣ የካቲት 26 2013ማስታወቂያ
በቀጣዩ አገር አቀፍ ምርጫ ተወዳዳሪዎች የምርጫ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የሚያስተላልፏቸው የፖለቲካ መልዕክቶች ከጥላቻ እና ቀስቃሽ ይዘቶች እንዲቆጠቡ ተጠየቀ ። የፀረ ጥላቻ ንግግር እና ሐሰተኛ መረጃዎች ሕግም ያለምንም አድሎ እንዲተገበር ዛሬ በአዲስ አበባ በተደረገ አንድ ውይይት ላይ ተጠይቋል።በኢትዮጵያ የምርጫ ታሪክ በዚህ ዓመት የሚከናወነው በአሉታም ሆነ በአዎንታ የማሕበራዊ መገናኛዎች ተፅዕኖ የሚነካው በመሆኑ ከጥላቻ እና ግጭት ቀስቃሽ መረጃና መልዕክቶች ስርጭት ሁሉም እንዲጠበቅ ያስፈልጋል ተብሏል።
ሰለሞን ሙጬ
ታምራት ዲንሳ
ማንተጋፍቶት ስለሺ