ምርጫ በኖርድራይንቬስትፋለን
ማክሰኞ፣ መጋቢት 11 2004ማስታወቂያ
ከሆላንድና ከቤልጂግ በሚዋሰነው በምዕራባዊው የጀርመን ፌደራል ክፍለ ግዛት ኖርድ ራይን ቬስትፋለን የፊታችን ግንቦት ምክር ቤታዊ ምርጫ ተጠርቷል ። ለጀርምን ጥምር መንግሥት ህልውና ወሳኝ የተባለው ይህ ምርጫም እዚህ ጀርመን ትኩረት ከተሰጣቸው አብይ ጉዳዮች አንዱ ነው ። ራድዮ ጣቢያችን ያለበት የቦን ከተማ የሚገኝበት ኖርድ ራይን ቬስትፋለን ከሌሎቹ ክፍለ ግዛቶች ጋር ሲነፃፀር በህዝብ ብዛት የመጀመሪያውን ደረጃ ይይዛል ። ይህም የዛሬ 2 ወሩ ምርጫ ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው ካደረጉት ምክንያቶች አንዱ መሆኑን የፍራንክፈርቱ የፖለቲካ ሳይንስና የህግ ምሁር ዶክተር ለማ ይፍራሸዋ ያሰረዳሉ ። የዛሬው አውሮፓና ጀርመን ዝግጅታችን ምርጫው የሚካሄድበትን ምክንያትና ውጤቱ በጥምሩ መንግሥት ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ ይቃኛል ።
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ