1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአቶ አራርሶ ቢቂላ የሚመራው ኦነግ በምርጫ የመሳተፍ ፍላጎት እንዳለው ገልጿል

ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 30 2013

በአቶ አራርሶ ቢቂላ የሚመራዉ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) መጋቢት አራት ቀን 2013 ዓ. ም ተቀመጥኩ ያለውን ድርጅታዊ ጠቅላላ ጉባኤ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ዉድቅ ያደረገው ያለአግባብ ነው ሲል የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ፍትሐ ብሔር ችሎት ዉሳኔ ማሳለፉን ፓርቲው አስታወቀ። 

Äthiopien Addis Abeba | OLF Anführer Qejela Meredasa, Birhanu Lema Tekedami , Ararso Biqila und Gelana
ምስል Seyoum Getu/DW

በአቶ አራርሶ ቢቂላ የሚመራው ኦነግ በምርጫ የመሳተፍ ፍላጎት እንዳለው ገልጿል

This browser does not support the audio element.

በአቶ አራርሶ ቢቂላ የሚመራዉ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) መጋቢት አራት ቀን 2013 ዓ. ም ተቀመጥኩ ያለውን ድርጅታዊ ጠቅላላ ጉባኤ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ዉድቅ ያደረገው ያለአግባብ ነው ሲል የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ፍትሐ ብሔር ችሎት ዉሳኔ ማሳለፉን ፓርቲው አስታወቀ። 
በጉባኤው የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ሆነው መሾማቸዉን የሚገልፁት የኦነግ አመራር አቶ ቀጄላ መርዳሳ ለዶቼ ቬለ እንዳሉት ፍርድ ቤቱ ትናንት ባስተላለፈዉ ዉሳኔ ቦርዱ ከዚህ ቀደም ያስተላለፈባቸዉን ዉሳኔ ሽሯል። 
አቶ ቀጄላ አክለው እንዳሉት ቦርዱ የፍርድ ቤቱን ዉሳኔ በፍጥነት ተግባራዊ ካደረገ ሊደረግ አንድ ወር እንኩአን ባልቀረው 6ኛ ብሔራዊ ምርጫ ላይ ለመወዳደር ፍላጎት አላቸዉ::
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከዚህ በፊት መጋቢት 4 የአመራር ቡድኑ የተቀመጠው ጠቅላላ ጉባኤ አግላይ እና ሁሉንም አመራሮች ባሳተፈ ሂደት ያልተደረገ በመሆኑ ዉድቅ ነው ማለቱ አይዘነጋም። ዶቼ ቬለ በከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ተላልፏል ስለተባለው ዉሳኔ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ አስተያየት ለመጠየቅ ያደረገዉ ሙከሪያ ለዛሬ አልተሳካም። 

ስዩም ጌቱ
እሸቴ በቀለ
ታምራት ዲንሳ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW