1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ምርጫ ቦርድ የዎላይታ ህዝበ ውሳኔን ውድቅ ማድረጉ

ሐሙስ፣ የካቲት 23 2015

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥር 29 ቀን በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት ውስጥ በሚገኙ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች ካካሄደው ሕዝበ ውሳኔ መካከል በዎላይታ ዞን የተከናወነው ውድቅ አደረገ።

Logo Äthiopiens Nationale Wahlbehörde
ምስል Ethiopian National Election Board

የምርጫ ቦርድ ውሳኔ

This browser does not support the audio element.

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥር 29 ቀን በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት ውስጥ በሚገኙ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች ካካሄደው ሕዝበ ውሳኔ መካከል በዎላይታ ዞን የተከናወነው ውድቅ አደረገ። ቦርዱ ሕዝበ ውሳኔው የምርጫ ሂደቱን ተዓማኒነት እና እውነተኛነት ያሳጣ ችግር የገጠመው መሆኑን በመግለጽ በዞኑ የመራጮች ምዝገባ እና የድምፅ አሰጣጡ በድጋሚ እንዲደረግ ወሰነ።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሕዝበ ውሳኔ ባካሄደባቸው ሌሎች አምስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (ከዎላይታ ዞን በስተቀር) የሕዝበ ውሳኔው ውጤት አዲስ ክልል እንዲመሰረት የሚያስችል ድምፅ የተሰጠበት መሆኑን ትናንት ይፋ ያደረገው መረጃ አመላክቷል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሕዝበ ውሳኔ ሂደቱ በዎላይታ ዞን እና በሌሎች ዞን እና ወረዳዎች «የወረዳ እና የቀበሌ አመራሮች ሕገ ወጥ የመራጮች ምዝገባ እንዲፈፀም ጫና ማድረግ፣ ለመራጭነት ብቁ ያልሆኑ ዜጎች ተመዝግቦ መገኘት እና ሌሎች የሕግ ጥሰቶች» ተፈፅመው እንደነበር ማረጋገጡንም ገልጿል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግሥት ውስጥ በሚገኙ ስድስት ዞኖች ( ኮንሶ ፣ ደቡብ ኦሞ ፣ ዎላይታ፣ ጋሞ ፣ ጌዴኦ እና ጎፋ ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች ( ቡርጂ፣ ባስኬቶ ፣ አሌ፣ አማሮ እና ደራሼ ) በአንድ የጋራ ክልል መደራጀት አንደግፍም የሚሉ ዜጎች የጎጆ ቤት ምልክትን እንዲመርጡ፣ እንዲሁም የጋራ ክልል መደራጀትን እንደግፋለን የሚለውን የሚደግፉ ደግሞ የነጭ እርግብ ምልክትን እንዲመርጡ ተደርጓል።
በዚህም መሠረት የዎላይታ ዞን የሕዝበ ውሳኔ ውጤት እና በሌሎች ዞን እና ልዩ ወረዳዎች ውጤታቸው ያልተካተተ 81 ጣቢያዎችን ሳይጨምር ቦርዱ ሕዝባ ውሳኔውን ባካሄደባቸው ሌሎች አምስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች የሕዝበ ውሳኔው ውጤት አዲስ ክልል እንዲመሰረት የሚያስችል ድምፅ የተሰጠበት የሕዝብ ውሳኔ አብላጫ ሆኖ ተመዝግቧል።የደቡብ ሕዝበ ውሳኔ ውጤት ምን ገጠመው?

የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

ከፍተኛ ችግር፣ እና ጥሰት የተስተዋለበት የተባለው የዎላይታ ዞን ሕዝባ ውሳኔ ግን ውድቅ ተደርጎ ምዝገባውም ሆነ ድምፅ አሰጣጡ በድጋሚ እንዲደረግ በቦርዱ ተወስኗል።
የቦርዱን የውጤት ዘገባ ያቀረቡት ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብሸት አየለ ናቸው። በመራጮች ምዝገባ ወቅት የሕግ ጥሰት በተፈፀመባቸው 24 የምርጫ ጣቢያዎች ላይ የተካሄደ ምዝገባ ተሰርዞ በድጋሚ የመራጮች ምዝገባ እንዲካሄድ መደረጉን ያስታወቀው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አጥፊዎቹ ተጠያቂ እንዲሆኑ ለፌደራል ፖሊስ አቤት ማለቱንም ገልጿል። ሌሎች በርከት ያሉ ችግሮች ገጥመውት እንደነበርም አስታውቋል። እንደገና እንዲደረግ ውሳኔ የተላለፈበት የወላይታ ዞን ሕዝበ ውሳኔ መቼ ይደረጋል የተባሉት የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚዴቅሳ ይህንን አሁን መመለስ እንደማይቻል እና ለሥራውም ተጨማሪ የበጀት ጥያቄ አለማቅረባቸውንም ገልጸዋል። ቦርዱ ይህንን ሥራውን ለማከናወን ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተፈቀደለትን በ435 ሚሊዮን መጠቀሙን እና ውጤቱን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት እንደሚያቀርብም አስታውቋል።

ሰሎሞን ሙጬ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW