1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ስፖርትሰሜን አሜሪካ

ምባፔ እና ሃላንድ የየራሳቸውን የታሪክ ገጾች መግለጥ ቀጥለዋል

ረቡዕ፣ ሰኔ 24 2018

የ2026ቱ የዓለም ዋንጫ የ32ቱ ቡድኖች የጥንካሬ መፈተኛ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ትናንት ማክሰኞ ምሽት በተደረጉ ጫወታዎች የዘመናችን ከዋክብቶች ኪሊያን ምባፔ እና አርሊንግ ሀላንድ ለየሀገሮቻቸው አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የከፈቱበት ተአምራዊ ምሽት ሆኖ አልፏል።

ምባፔ በስዊዲን ላይ ሁለት ጎሎችን አስቆጥሯል
ምባፔ በስዊዲን ላይ ሁለት ጎሎችን አስቆጥሯልምስል፦ Al Bello/Getty Images/AFP

ምባፔ እና ሃላንድ የየራሳቸውን የታሪክ ገጾችን መግለጥ በቀጠሉበት የዓለም ዋንጫ ማንኛቸው ይነግሱ ይሆን?

 
የ2026ቱ የዓለም ዋንጫ የ32ቱ ቡድኖች የጥንካሬ መፈተኛ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ትናንት ማክሰኞ ምሽት በተደረጉ ጫወታዎች  የዘመናችን ከዋክብቶች ኪሊያን ምባፔ እና አርሊንግ ሀላንድ ለየሀገሮቻቸው አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የከፈቱበት ተአምራዊ ምሽት ሆኖ አልፏል። ፈረንሳይ፣ ኖርዌይ እና አስተናጋጇ ሜክሲኮ አስደናቂ ድሎችን አስመዝግበው ወደ ቀጣዩ ዙር ተሸጋግረዋል።


ምባፔ የዓለም ዋንጫውን የታሪክ መዝገብ በአዲስ መልክ ፅፏል


በምስራቅ ራዘርፎርድ በተደረገው ጨዋታ ፈረንሳይ ስዊድንን 3 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት በመርታት የውድድሩ ጠንካራ ተፎካካሪነቷን አስመስክራለች። ጨዋታው ሙሉ በሙሉ በፈረንሳዩ አምበል ኪሊያን ምባፔ  ድንቅ ችሎታውን ያሳየበት እና ከአርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ ጋር ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነቱን ፍክክር ከፍ ያደረገበትን ምሽት ሆኖ አልፏል። 
ምባፔ በ45ኛው እና በ74ኛው ደቂቃ ላይ ሁለት አስደናቂ ግቦችን በማስቆጠር በዓለም ዋንጫየማጣሪያ እና የጥሎ ማለፍ  ታሪክ 10 ግቦችን በማግባት የመሪነቱን ክብረ ወሰን ብቻውን ጨብጧል። በ27 ዓመቱ በዓለም ዋንጫዎች ላይ ያስቆጠራቸውን አጠቃላይ ግቦች 18 ማድረስ ሲችል  የሊዮኔል ሜሲን (19 ግቦች) የምንግዜም የዓለም ዋንጫ ግቦች ክብረ ወሰን ለመጋራት አንድ ግብ ብቻ ነው የሚቀረው። በጨዋታው ላይ ብራድሌይ ባርኮላም ሌላኛዋን ግብ አክሏል። ደማቅ ሰማያዊዎቹ በ16ቱ የጥሎ ማለፍ ውድድር ጀርመንን ጥላ ካለፈችው  ከፓራጓይ ጋር በፊላደልፊያ ይገናኛሉ። 

ምባፔ የዓለም ዋንጫውን የታሪክ መዝገብ በአዲስ መልክ ፅፏልምስል፦ Björn Larsson Rosvall/TT/picture alliance


 በሀላንድ አስደናቂ ግብ ኖርዌይ ለመጀመሪያ ጊዜ ታሪክ ሰርታለች


በዳላስ  በተደረገው ጨዋታ ኖርዌይ አይቮሪ ኮስትን  2 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍበዓለም ዋንጫታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የጥንካሬ መፈተኛ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ማሸነፍ ችላለች።
ጨዋታው በሁለቱም በኩል በነበረው ብርቱ ፉክክር 1 ለ 1 ተመጣጣኝ ሆኖ ፤የኖርዌይን የመጀመሪያ ግብ አንቶኒዮ ኑሳ ሲያስቆጥር፣ ለአይቮሪኮስት ደግሞ አማድ ዲያሎ አቻ አድርጎ ነበር። ቻወታው ሊጠናቀቅ ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀሩት፣ በ86ኛው ደቂቃ ላይ ተአምረኛው አጥቂ አርሊንግ ሀላንድ  የኖርዌይን ታሪካዊ አሸናፊነት ያረጋገጠችውን ወሳኝ ግብ አስቆጥሯል። ግቧ ሀላንድ በውድድሩ ላይ ያስቆጠራት 5ኛ ግብ ሆና ስትመዘገብለት ፣ ለሀገሩ ኖርዌይ በ53 ጨዋታዎች ብቻ 60ኛ ዓለም አቀፍ ግቡን በማስቆጠር በእግር ኳስ ታሪክ ይህንን ቁጥር በፍጥነት የደረሰ የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል።

ኖርዌይ በ16ቱ ዙር ከአምስት ጊዜው የዓለም ሻምፒዮን ብራዚል ጋር ከባድ ፍልሚያ ይጠብቃታል። ተሸናፊዋ አፍሪቃዊቷ አይቮሪኮስት በምድብ ጫወታዎች ያሳየችውን ብቃቷን አለመድገሟ ፣ በጫወታው ወቅት የተፈጠሩ የጎል ዕድሎችን በአግባቡ አለመጠቀሟ ብሎም ተጫዋቾቹ በመጨረሻ ትኩረት ማጣታቸው ለሃገራቸው ብሎም ለተተቀረው ደጋፊ አፍሪቃዉኢኑ ልብ ሰባሪ ሆኗል። 

በሀላንድ አስደናቂ ግብ ኖርዌይ ለመጀመሪያ ጊዜ ታሪክ ሰርታለችምስል፦ Tony Gutierrez/AP Photo/picture alliance


ሜክሲኮ የ40 ዓመት እርግማኗን በኤስታዲዮ አዝቴካ ሰብራለች


በሜክሲኮ ሲቲ በሚገኘው ታሪካዊው ኤስታዲዮ አዝቴካ  ስታዲየም፣ አስተናጋጇ ሜክሲኮ ኢኳዶርን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት በመርታት በደጋፊዎቿ ፊት ትልቅ ታሪክ ሰርታለች። ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት በነበረው መብረቅ እና ከባድ ዝናብ ምክንያት ለጥቂት ጊዜ ዘግይቶ የነበረ ቢሆንም፣ የሜክሲኮ ደጋፊዎች ስታዲየሙን በደመቀ ሁኔታ ሞልተውት  ነበር።
 ድሉ ሜክሲኮ ከ1986ቱ የዓለም ዋንጫበኋላ ማለትም ከ40 ዓመታት በኋላ በዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ላይ ያገኘችው የመጀመሪያው ድል ነው። ጁሊያን ኩዊኖነስ  በ22ኛው ደቂቃ ላይ አስደናቂ ግብ አስቆጥሮ ሜክሲኮን መሪ  ሲያደርግ ከ9 ደቂቃዎች በኋላ ደግሞ አንጋፋው አጥቂ ራውል ጂሜኔዝ ሁለተኛውን ግብ እንዲያስቆጥር አመቻችቶለታል። ሜክሲኮ ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ ምንም ግብ ሳታስተናግድ ጉዞዋን ስትቀጥልቀጣይ ተጋጣሚዋን ለማወቅ የእንግሊዝ እና የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን ጨዋታ ትጠብቃለች።

ሜክሲኮ የ40 ዓመት እርግማኗን በኤስታዲዮ አዝቴካ ሰብራለችምስል፦ Takuya Matsumoto/AP Photo/picture alliance


          ልብ አንጠልጣይ ጥያቄዎች


የዓለም ዋንጫ አሁን ላይ ወደ ተለየ የክብር እና የፉክክር ምዕራፍ ተሸጋግሯል። የሊዮኔል ሜሲ እና የክርስቲያኖ ሮናልዶ ዘመን ማክተምን ተከትሎ፣ የዓለም እግር ኳስን በበላይነት ለመምራት የሚደረገው ፍልሚያ አሁን በፈረንሳዩ ንጉስ ኪሊያን ምባፔ እና በኖርዌዩ የግብ ማሽን አርሊንግ ሀላንድ መካከል በግልፅ እየታየ ነው። ምንም እንኳ ሊዮኔል ሜሲ አሁንም በአስደናቂ አቋሙ ላይ ቢገኝም። 


ማን ይሆን የውድድሩ ኮከብ ሆኖ የሚወጣው? 


ምባፔ በዓለም ዋንጫው ታሪክ የነገሰበትን የጥሎ ማለፍ  ሪከርድ ይበልጥ አድሶ ፈረንሳይን ወደ ሌላ የከበረ ዋንጫ ይመራታል? ወይስ ሀላንድ ለሀገሩ የጀመረውን ታሪካዊ ጉዞ በመቀጠል፣ በግል ብቃቱ ውድድሩን ጠቅልሎ በመውሰድ የወርቅ ጫማውን እና የዓለም ዋንጫውን ኮከብነት ክብር ይነጥቃል? የሁለቱ ኮከቦች ትንቅንቅ መላውን ዓለም በጉጉት እያስጠበቀ ይገኛል። ነው ወይስ አሁንም የእግር ኳሱ ድንቅ ሊዮኔል ሜሲ ክብሩን አሳልፎ ላለመስጠት ሀገሩን ዳግም ለክብር ያበቃ ይሆን ?

ማን ይሆን የውድድሩ ኮከብ ሆኖ የሚወጣው? ምስል፦ Sam Hodde/AP Photo/picture alliance


        ሜክሲኮስ ከአዘጋጆቹ በተሻለ ሁኔታ ትገፋ ይሆን? 


ሜክሲኮ የ40 ዓመት የጥሎ ማለፍ እርግማኗን የሰበረችበት እና በኤስታዲዮ አዝቴካ ያሳየችው የአሸናፊነት ወጥነት ትልቅ ተስፋን ጭሯል። ከሌሎቹ የውድድሩ ተባባሪ አዘጋጆች (አሜሪካ እና ካናዳ) በተሻለ ሁኔታ የደጋፊዎቿን ስሜት እና የሜዳዋን ምቹነት ተጠቅማ እስከ ፍፃሜው ድረስ አስገራሚ ጉዞ ታደርግ ይሆን? ወይስ በቀጣዩ ዙር ከባድ ፈተና ይጠብቃታል?

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW