ምክር ቤት ያልተቀበለው የፈረንሳይ የስደተኞች ሕግ ማሻሻያ
ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 2 2016
የፈረንሳይ መንግሥት ያዘጋጀውን የስደተኞች ሕግ ማሻሻያ የሚቃወም የውሳኔ ሀሳብ ላይ ትናንት ድምጽ የሰጠው የሀገሪቱ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የውሳኔ ሀሳቡን በመደገፍ ማሻሻያውን ሳይቀበለው ቀርቷል። ማሻሻያው ያላለፈው የግራም ሆነ የቀኝ ፖለቲካ የሚያራምዱ ተቃዋሚ የምክርቤት አባላት በሙሉ የውሳኔ ሀሳቡን ደግፈው ድምጻቸውን በመስጠታቸው ነው። የመሀል አቋም ያለው የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት የኢማኑኤል ማክሮ መንግሥት በምክር ቤቱ አብላጫ ድምጽ የለውም።በዚህ የተነሳም በተደጋጋሚ ጊዜያት እንዳጋጠመው የውሳኔ ሀሳቡ በ270 የድጋፍና በ265 የተቃውሞ ድምጽ ሊያልፍ ችሏል።
መንግሥት ማሻሻያው ወደሀገሪቱ የሚካሄድ ስደትን የመቆጣጠርና ስደተኞችም ከቀድሞው በተሻለ ከኅብረተሰቡ ጋር እንዲዋሀዱ የማድረግ ዓላማ አለው ይላል። ሕጉ ፣ አምስት ዓመትና ከዚያ በላይ እስር የተፈረደባቸውን ስደተኞች ከፈረንሳይ ማባረርን ለመንግሥት ቀላል ያደርግለት ነበርም ተብሏል።
ይሁንና የግራ አቋም አራማጅ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በማሻሻያው የተካተቱት እርምጃዎች ሲበዛ ጨቋኝ ናቸው ሲሉ ቀኞቹ ደግሞ ሕጉ ያን ያህል ጠንካራ አይደለም በማለት አጣጥለውታል። ሕጉ የስደተኞች ቤተሰቦችን ወደ ፈረንሳይ ማምጣቱን ከባድ ያደርገዋል። የፈረንሳይ ሁከትየፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩ አቶ ፉአድ ኢስማኤል ከማሻሻያው ዋነኛ ዓላማዎች አንዱ ሌሎች የአውሮጳ ሀገራት ስደተኞች በብዛት እንዳይመጡባቸው እንደሚወስዷቸው እርምጃዎች ሁሉ ፈረንሳይም የሚመጡባትን ስደተኞች ቁጥር መቀነስ መሆኑን ያስረዳሉ። ይህን ዓላማ ለማሳካትም ሕጉ የስደተኞች መሻገሪያ ከሆኑ ሀገራት ጋር ስምምነት ለመፍጠርም እንዲያመች ተደርጎ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።
ምንም እንኳን ፈረንሳይ ወደ ሀገርዋ የሚመጡ ስደተኞችን ቁጥር ለመቀነስ ያስችላል ያለችውን ሕግ ብታዘጋጅም ወደፊት እድሜው የገፋ የኅብረተሰብ ክፍል እንደሚያመዝንባት የታወቀ ሀገር በመሆንዋ ከውጭ የሚገባ የሰው ኃይል በእጅጉ እንደሚያስፈልጋት ተደጋግሞ ይነገራል። በጉልበት ስራም ይሁን በሌሎች የውጭ ዜጎች በሚፈለጉባቸው የስራ መስኮች ያሉ ክፍተቶችን ለመሙላት ስደተኞችን ማስገባቱ ጠቃሚ ሆኖ ሳለ ለምን ይሆን መንግሥት ከዚህ በተቃራኒ ወደ ፈረንሳይ የሚመጡ ስደተኞችን ቁጥር ለመገደብ ያሰበው? ፈረንሳይ የተማሩት የሰሩትና የሚኖሩት አቶ ፉአድ ኢስማኤል የዚህን ምክንያት የተደበላለቀ ሲሉ ገልጸውታል።
ረቂቁ ሕግ የተገን አሰጣጥ ሂደትን የሚያፋጥን ፣ ስደተኖች አቤቱታ የሚያቀርቡበትን ጊዜን የሚያሳጥር ከቤተሰባቸው ጋር የሚቀላቀሉበትን ሂደት ይበልጥ የሚያወሳስብ እንዲሁም ሰዎች ለህክምና ወደ ፈረንሳይ የሚመጡበትን እድል የሚገድብ ነው ።ማክሮ ከአመጹ በኋላ 'መሰረታዊ መልሶች' ለመስጠት ቃል ገቡየፈረንሳይ መንግሥት ከዚህ ቀደም በጉልበት ስራ ለተሰማሩ ስደተኞች የአንድ ዓመት የመኖሪያና የስራ ፈቃድ የመስጠት እቅድ ነበረው ።አሁን ግን የአንድ ዓመት የመኖሪያና የስራ ፈቃድ የመስጠቱን ውሳኔ ለየግዛቶች ባለሥልጣናት አስተላልፏል። ታዲያ በዚህ ሳምንት በፈረንሳይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሊያልፍ ያልቻለው አዲሱ የስደተኞች ሕግ እጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል? አቶ ፉአድ ሊሆኑ ይችላሉ ያሏቸውን ሦስት ሁኔታዎች ገልጸዋል።
የኢማኑኤል ማክሮ ገዥ ፓርቲ ከፍተኛ ባለስልጣን ከዚህ ቀደም እንደተናገሩት መንግሥት ወንጀል ፈጽመዋል የተባሉ ወደ4ሺህ የሚጠጉ ሕገ ወጥ የሚላቸውን ስደተኞች በየዓመቱ ማባረር አለበት። ለውጥ በተደረገበት በአዲሱ ሕግ እነዚህን ስደተኞች ማባረሩ አንድ ዓመት ብቻ ነው የሚፈጀው አሁን በሚሰራበት ሕግ ግን ሁለት ዓመት ይወስዳል። ከዚህ ጎን ለጎን መንግሥት የተሻሻለው ሕግ ወደ ፈረንሳይ ለስራ መምጣት የሚፈልጉ ሰዎችን ይበልጥ የሚስብ ነው ይላል። ዶቼቬለ የጠየቃቸው የግል ድርጅቶች ያሏቸው አሰሪዎች መንግስት ከዚህ ቀደም ለስደተኞች ቢያንስ የአንድ ዓመት የስራና የመኖሪያ ፈቃድ ለመስጠት አውጥቶት የነበረውን እቅድ ስራ ላይ እንዲያውል ይፈልጋሉ።የፈረንሳይ የጡረታ ደንብ ማሻሻያ የገጠመው ተቃውሞ አንድ የምግብ ቤት ባለቤት እንዳሉት ቡና ቤቶችና ምግብ ቤቶች ካለውጭ ዜጎች ስራቸውን ማካሄድ አይችሉም። በእርሳቸው አባባል በፈረንሳይ በዚህ ዘርፍ ከተሰማራው የሰው ኃይል አንድ አራተኛው የውጭ ዜጋ ነው። በፈረንሳይ የውጭ የሰራተኛ ኃይል የሚያስልገው በተለይ የፈረንሳይ ወጣት ትውልድ ጉልበት የሚያሻቸው ከባድ ስራዎች መስራት ባለመፈለጉ መሆኑን የምግብ ቤቱ ባለቤት ተናግረዋል።ከዚያ ይልቅ የወጣቱ ፍላጎት በዲጂታል የሥራ ዘርፍ መሰማራት ነው ብለዋል። አቶ ፉአድም የውጭ ሰራተኞች ለሀገሪቱ ኤኮኖሚ እድገትም እንደሚያስፈልጉ ጠቅሰዋል።
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ