ምዕራብ ወለጋ ዞን በዚህ ሳምንት አራት ሰዎች ተገደሉ
ረቡዕ፣ ጥር 21 2017
በምዕራብ ወለጋ ሁለት ወረዳዎች የ4 ሰዎች ሕይወት አልፏል።
ለዓመታት በግጭት ውስጥ ከቆየው የምዕራብ ኦሮሚያ ዞኖች መካከል ምዕራብ ወለጋ ውስጥ የሚከሰቱት ጸጥታ ችግሮች የነዋሪውን እንቅስቃሴ መገደብን ጨምሮ በጤና ተቋማት ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ማሳደሩን የአካባቢው ነዋሪዎች እና የጤና ባለሙያዎች ሲናገሩ ቆይተዋል፡፡ በዚህ አካባቢ በጸጥታ ሀይሎች እና ሸማቂዎች መካከል ግጭት በተለያየ ወቅቶች እንደሚሰከቱና በግጭት ውስጥ ያልተሳተፉ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት እየደረሰ እንደሚገኙ ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ በዞኑ ባቦ ጋምቤል ወረዳ ደግሞ ጴጥሮሰ ፍቅሩ የተባሉና ሌላው አንድ ሰላማዊ ነዋሪ ሰሞኑን ከታጣቂዎች ጋር ግንኙት አላችሁ በማለት በጸጥታ ሐይሎች ተይዘው መገደላቸውን አንድ የበተሰባቸው አባል ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም አሊይ የተባሉ የወረዳው ነዋሪው እንደዚሁ ከታጣቂዎች ጋር ግንኙነት አላህ በማለት በትናንትናው ዕለት በደረሰበት ድብደባ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት ጠቁመዋል፡፡
ምዕራብ ወለጋ አንዳንድ ወረዳዎች ኤሌክትሪክ እንደተቋረጠ ነው
‹‹ አሊይ ያደታ የተባለ በባቦ ጋምቤል ፖሊስ ጣቢያ ከታሰረ በኃላ ብዙ ጊዜ ድብደባ ተፈጽሞበት ተጎድ አሁን መናገር አይችልም፡፡ መልካ ኤቢቻ በተባለ ቦታ ደግሞ ጴጥሮስ ፍቅሩ የተባለ አንድ ሰው ተይዘው ተገድለዋል፡፡ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ትቀልባለህ ፣ትደግፍለህ በማለት ነው የተገደለው፡፡ ሰው በጸጥታ ችግርም በጤና በኩልም እየተቸገረ ነው፡፡›› በማለት በአካባቢው የጸጥታ ችግር እያሳደረ ያለውን ተጽህኖ አብራርተዋል፡፡ በዚህ ጉዳይም ላይ መረጃ እንዲሰጡን የጠቅናቸው የባቦ ጋምቤል ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ በንቲ ቶሊና በጸጥታ ሐይሎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል መባሉን እና ሰው ህይወት ማለፉን ካስተባበሉ በኃላ ጉዳዩን እንደገና ማጣራት እንዳለባቸው እና ከቀኑ ሰባት ሰዓት እንዲደውልላቸው በመናገር ስልካቸውን ዘግተዋል፡፡ በተባለው ሰዓት መልሰን ብንደወልላቸውም ሰልካቸው ዝግ ነው፡፡
በዞኑ ቅልቱ ካራ ወረዳ ባለፈው ቅዳሜ የሰው ሕይወት አልፏል
በምዕራብ ወለጋ ዞን ቅልቱ ካራ ወረዳ ደግሞ ባለፈው ቅዳሜ ጠዋት 2 ፡00 ሰዓት ገደማ ወደ 3 ሰዎች ተዘይዘው በአካባቢው የሚንቀሳቀሰውን ታጣቂዎችን ደግፋቹሀል በሚል 2ቱ ሲገደሉ አንድ ሰው ደግሞ በደረሰበት ድብደባ በመጎዳት የህክምና እርዳታ እየሰተደረገለት እንደሚገኝ ያነጋርናቸው የአካባቢው ነዋሪዎች አመልክተዋል፡፡ « ቅዳሜ ጠዋት 3 ሰዎችን ወደ ስራ እየዱ እያሉ ይዘው እጃቸውን ወደኃላ በማሰር በአንድ ትምህርት ቤት አካባቢ አለፍ ብለው ሁለቱ በጥይት ተመተው ሲሞቱ አንዱ ሁለት ቦታ ተመጥቶ ተርፈዋል፡፡ ሼኔ ትቀልባላቹ ታግዛላቹ በሚል የተያዙት፡፡ ከተያዙት መካከል ስማቸው ሁለቱ ጋርህ ባህሩ እና ማቲ ቡልቻ ሲሆኑ ገበየው ተሸሜ የተባለው ደግሞ በሁለት ጥይት ተመተው በአሁኑ ጊዜ ለህኪምና እርዳታ ጤና ጣቢያ ይገኛል፡፡»
ምዕራብ ወለጋ፤ በፀጥታ ችግር የተዘጋዉ መንገድ ዳግም ሥራ ጀመረ
በወረዳው በዚህ ጥር ወር መጀመሪያ ላይ በአንድ ቦታ ከታጣቂዎች ጋር በተገናኙ የአምስት ሰዎች ህይወት ማለፉን ሌላው የአካባቢው ነዋሪ ተናግረዋል፡፡ በቅልቱ ካራ ወረዳ ተፈጸመዋል የተባለውን ሰላማዊ ሰዎች ጥቃት እና ህይወት ማለፈ ዙሪያ ማብራሪያ እንዲሰጡን የተጠየቅናቸው የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ተስፋ ፈይሳ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርቷል፡፡ የትጥቅ እንቅስቃሴ በሚስተዋልበት በምዕራብ ወለጋ እና ሌሎችም የሀገሪቱ አካባቢዎች ውስጥ የሰላማዊ ሰዎችም ግዲያና የንብረት ውድመት በተደጋጋሚ መከሰቱን በቅርቡ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ያወጣው ሪፖርትም ያመለክታል፡፡
ነጋሳ ደሳለኝ
ኂሩት መለሰ
ፀሐይ ጫኔ