ሦስተኛው የአውሮጳ ኅብረትና አፍሪቃ አገሮች የሚኒስትሮች ስብሰባ
ሐሙስ፣ ግንቦት 14 2017
ስብሰባውን የመሩት የኅብረቱ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ካያ ካላስና የአንጎላ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተርና የአፍሪቃ ኅብረት የሥራ አስፈጻሚ ካውንስል ሰብሳቢ ቴቴ አንቶኒዮ ናቸው።
ስብሰባው ያተኮረባቸው ጉዳዮችና ያስተላለፋቸው ውሳኔዎች
ሦስተኛው የአውሮጳ ኅብረትና የአፍሪቃ ኅብረት አባል አገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የጋራ ስብሰባ በዋናነት በስላምና ደህንነት፣ በጋራ ጉዳዮች ላይ አብሮ መሥራት ፤ የኢኮኖሚ እድገትና የስደተኞች ጉዳይ ዙሪያ ያተኮረ እንደነበር ተገልጿል። እንደ ጎርጎሪዮስ አቆጣጠር በ2000 ዓመተ ምህረት ካይሮ ላይ የተፈረመው የሁለቱ አህጉሮች የትብብርና አጋርነት ስምምነት ዘንድሮ 25 ዓመት የሞላው ሲሆን፤ ሚኒስትሮቶቹ በስብሰባቸው በተለይ እንደ አውሮጳ አቆጣጠር የካቲት 2022 በተካሂደው ስድስተኛው የመሪዎች ስብሰባ የተላለፉትን ውስኔዎች አፈጻጸም በጥልቀት እንደገመገሙ ተገልጿል። ትብብራቸውን የበለጠ ለማጠናከርና ወደላቀ ደረጃ ለማሳደግ የሚያስችሉ ውሳኔዎችን በማሳለፍና ባለ ዐሥር ገጽ የጋራ መግለጫ በማውጣት ሚኒስትሮቹ ስብሰባቸውን ያጠናቀቁ ሲሆን፤ ይህም በዚህ አመት መጨረሻ ለሚካሄደው የአፍርቃና አውሮጳ ኅብረት አገሮች ሰባተኛው የመሪዎች ጉባኤ ስኬት መሰረት ሊሆን እንደሚችል ታምኖበታል።
የኅብረቱ የውጭ ጉዳይ ኃላፊና የስብሰባው መሪ ያስተላለፉት መልዕክት
የኅብረቱ የውጭ ጉዳይ ኃላፊና የሰብሰባው መሪ ወይዘሮ ካያ ካላስ ሁለቱ አህጉሮች ሊነጣጠሉ የማይችሉና በጋራ ጥቅም የተሳሰሩ ስለመሆኑ በስብሰባው አንስተዋል ። «አፍሪቃና አውሮጳ መንታ አህጉሮች ናቸው። በጄኦግራፊ የምንገናኝ፤ የማንነጣጠል ነን» በማለት የጋራ ፍላጎትና ጥቅሞች እንዳሉን ሁሉ ሁለቱ አህጉሮች የጋራ ተግዳሮቶችና ፈተናዎችም እንዳሉባቸው ገልጸዋል።
አይይዘውም የውጭ ጉዳይ ኃላፊዋ አፍርካ አሉ በስብሰባው ላይ፤ "አፍርካ በማደግ ላይ ያለና በአለም የወጣቶች ቁጥር በፍጥነት እያደገበት ያለ አህጉር ነው” በማለት አህጉሩ በልዩ ልዩ ማዕድናትና ለአረንጉዴና ዲጂታል ቴክኖሎጂዎች ወሳኝ በሆኑ ጥሬ ዕቃዎች የታደለ መሆኑን በማንሳት ያውሮፓ ህብረት በአህጉሩ ዋናው ኢንቨስተር መሆኑን አስገንዘዋል ።
ወይዘሮ ካያ ከጉባኤው በኋላ በሰጡት መግለጫም የአውሮጳ ኅብረት አፍርቃ ሊተማመንበት የሚገባ አጋሩ መሆኑን አጽንኦት ስተው ተናግረዋል፤ "የአውሮፓ ህብረት የአፍርካ ሊተማመንበት የሚገባ አጋሩ ነው። በአህጉሩ ሰላምና ደህንነት እንዲሰፍን እየረዳን ነው” በማለትም በአውሮፓ የሰላም አመቻቺ (European peace facility) በኩል ለአፍርካ አጋሮች ከአንድ ቢሊዮን ኢሮ በlላይ እርዳታ የተለገሰ መሆኑን በመጥቀስ ፤ የአውሮጳ ኅብረት የአፍሪቃ አሰተምማኝ አጋር ሆኖ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
የስብሰባው ወቅታዊነትና ፋይዳው
ይሁን እንጂ የሁለቱ አህጉሮች ህብረትና ትብብር የሚባልለትን ያህል እንድላሆነ ነው ከብዙ አቅጣጫ የሚነገረው። ፤ በስደተኖች ጉዳያ ህብረቱ ስደተኖች ወደ አህጉሩ እንዳይገቡና እንዲመለሱ እንጂ የስደት ምክንያት በሆኑት ችግሮች ዙሪያ ብዙም እየሰራ እንዳላሆነ፤ በሰላምና ደህንነት ጉዳይም ህብረቱ በተመሳሳይ ትኩረት እየሰጠ አለመሆኑን ሱዳንን እንደማሳያ በመጥቀስ ጋዜጠኞች ወይዘሮ ክያን ጠይቀዋቸዋል።
ያም ሆኖ ግን ይህ የሁለቱ አህጉሮች የሚኒስትሮች ስብሰባ ወሳኝና ወቅታዊ መሆኑን ነው በአውሮጳና አፍሪቃ ግንኑነቶች ላይ የሚሠራውና የአውሮጳ የእድገት ማዕከል በእንግሊዥኛ ምህጻሩ (Ecdpm) የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት ወይዘሮ ካቲሊን ቫን ሆፍ በተለይ ለዲደብሊው የተናገሩት፤ ወይዘሮ ካቲሊን የህለቱ ግንኑነት የሚነገርለትን ያህል አለመሆኑን በመጥቀስ የአሁኑ የሚኒስትሮች ስብሰባ ግን ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል። ”ይህ ስብሰባ በትክክለኛ ጊዜ የተደረገ ይመስለኛል። በአውሮፓውያኑ በኩል ከሌላው አለም ይበልጥ ለአፍሪካ የተለየ ቀረቤታና ስሜት እንዳላቸው ማሳየት ይፈልጋሉ” በማለት በአለማቀፍ ደረጃ እየታዩ ካሉት ተግዳሮቶች አንጻር ይህ ስብሰባ የሁለቱን ግንኑነት ለማጠናከር ሊረዳ እንደሚችል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል ።
ገበያው ንጉሤ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ