ሩስያ የዶቼ ቬለን ቴሌቪዥን ዘጋች
ዓርብ፣ ጥር 27 2014
ማስታወቂያ
ሩስያ መቀመጫዉን ሞስኮ ላይ ያደረገዉን እና በሩስያ ቋንቋ የሚያሰራጨዉን የጀርመን ቴሌቭዥን ዶቼቬለን ስርጭት አቋረጠች። ይህ የሩስያ ርምጃ የተሰማዉ የጀርመን መንግሥት በያዝነዉ ሳምንት ረቡዕ ሩስያ ቱዴይ RT የተባለዉን በጀርመንኛ የሚያሰራጨዉን የሩስያን ዓለምአቀፍ የቴሌቭዥን ጣብያ መዝጋቱን ተከትሎ ነዉ። ሮይተርስ የዜና አገልግሎት የሩስያን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጠቅሶ ዛሬ እንደዘገበዉ ፤ ሩስያ በሃገሪቱ የሚገኘዉን የዶቼ ቬለን ቢሮ ትዘጋለች፤ የሰራተኞቹን ፈቃድም ትነጥቃለች።የጣብያዉ ስርጭት በሩስያ ግዛት እንዲቆም ይደርጋል። የጀርመን የመገናኛ ብዙኃን ተቆጣጣሪ ኮሚሽን በዚህ ሳምንት እንዳስታወቀው፣የሰርቢያን ፈቃድ ይጠቀማል ያለው በጀርመንኛ ቋንቋ የሚያሰራጨዉ የሩስያ ብዙኃን መገናኛ ሩስያ ቱዴይ RT ትክክለኛ ፈቃድ ስለሌለዉ መዘጋት አለበት። ይህን መግለጫ ተከትሎ ክሪምሊን በአፀፋዉ ሞስኮ የመከላከያ እርምጃን እንደምትወስድ አስጠንቅቆ ነበር።
አዜብ ታደሰ/ይልማ ኃይለሚካኤል
ኂሩት መለሰ