1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ሩብ ክፍለ ዘመን የደፈነው የአፍሪቃ እና የአውሮጳ ህብረት አጋርነት

ማክሰኞ፣ ግንቦት 19 2017

የአውሮፓ ህብረትና ያኔ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ይባል የነበረው የሁለቱ አህጉሮች የትብርና አጋርነት ስምምነት የተፈረመው የዛሬ ሀያ አምስት አመት እ እ እ በ200 ዓም ከሚያዚያ 3 - 4፤ ካይሮ ላይ በተደረገ የመሪዎች የጋራ ጉባኤ ነው። የትብብሩ ህያ አምስተኛ አመት አመቱን ሙሉ በሁሉም አገሮች በልዩ ልዩ ፕሮግራሞች እንደሚከበር ተገልጿል ።

EU-Afrika Gipfel in Lissabon, Portugal Flaggen der europäischen und afrikanischen Nationen, die bei dem Gipfel vertreten sind Symbolbild
ምስል፦ AP

የአውሮጳ ህብረት እና አፍሪቃ የረዥም ዓመታት የአጋርነት ታሪክ እና አንድምታው

This browser does not support the audio element.

የአውሮፓ ህብረትና አፍሪካ የ25 አመት አጋርነት

የአውሮፓ ህብረትና ያኔ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ይባል የነበረው የሁለቱ አህጉሮች የትብርና አጋርነት ስምምነት የተፈረመው የዛሬ ሀያ አምስት አመት እ እ እ በ200 ዓም  ከሚያዚያ 3 እስከ 4፤ ካይሮ ላይ በተደረገ የመሪዎች የጋራ ጉባኤ ነው። የትብብሩ ህያ አምስተኛ አመት አመቱን ሙሉ በሁሉም አገሮች በልዩ ልዩ ፕሮግራሞች እንደሚከበር ተገልጿል ። ትብብሩ በሁለቱም አህጉሮች የሚኖሩትን  1.9 ቢሊዮን  ህዝቦች ተስፋ ስንቆ፤ እድገትና ብልጽግና አልሞ  በህዝቦች የጋራ እሴቶችና ፍላጎቶች ላይ እንድተመሰረተና ለባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲም ክፍት ሆኖ እንደተቋቋመ የትብብሩ የምስረታ ታሪክ ያስረዳል። በሁለቱ ህብረቶች መካለክል የተደረስው የፖለቲካ ስምምነትና ትብብር ለሁለቱም ወገኖች የኢኮኖሚ እድገት፤ የባህልና የፖለቲካ ትሥሥር ከፍተኛ አስተዋጾ አድርጓል።

ከአጋርነት ምስረታው በኋላ የተካሂዱ ጉባኤዎችና የተላለፉ ውሳኔዎች

ከካይሮው የምስረታ ጉባኤ በኋላ በየግዜውና በየደረጃው የተደረጉ ጉባኤዎችና የወጡ  መርሀ ግብሮች ትብብሩ እንዲያድግና  ውጤታማ እንዲሆን ረድተዋል።  እ እ እ በ2007 አመተ ምህረት ሊስቦን ላይ የተካሄደው የመሪዎች ጉባኤ የአፍሪካ ህብረትን ምስረታም አስከትሏል። የአፍሪካና የአውሮፓ ህብረት የጋራ ስትራቴጂ የጸደቀበትና የረጅም ግዜ የትብብር ፕሮግራምም የተነደፈው በዚሁ ወቅት ነበር።

የአፍሪቃ አውሮጳ ሕብረት ጉድኝት

 እ እ እ በ2010 ዓም ሊቢያ ትሪፖሊ ላይ የተካሄደው ጉባኤ መሪ ቃል ደግሞ  `አፍርካና የአውሮፓ ህብረትን ማገናኘት` የሚል የነበር ሲሆን  በዘላቂ ልማት የሚደረገውን ትብብር ለማጠናከር የተግባር እቅድ የወጣበትና የተባበሩት መንግስታት እየር ነበረት ስምምነትንና የቶኪዮውን ፕሮቶኮልን በሚመለክት የጋራ መግለጫ ወይም ዲክላሬሸን የወጣበት ነበር፤ ምንም እንኳ ከዚያ ወዲህ ሊቢያ  ሙሉ በሙሉ  እንደአገር ቀጥላለች ማለት ባይቻልም።  

 እ እ በ2014 አም በበራስልስ ቤልጅየም የነበረው አራተኛው ጉባኤ ከጉባኤዎቹ ሁሉ ትልቁና ክዘጠና በላይ  ለኡካን የተካፈሉበት እንደነበር  ይጠቀሳል። ። በዚህ ጉባኤ በተለይ ወጣቶችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የኢኮኖሚና የሰው ሀይል እድገት ላይ ያተኮሩ አጀንዳዎች ትኩረት እንደተደረገባቸውና የአውሮፓ ህብረትና ያፍሪካ ግንኙነት ፍኖተ ካርታ የተዘጋጀበት እንደሆነም ይነገራል።

 በ2017 አም ኮቲዲቩዋር የተደረገው ጉባኤም እንደዚሁ ወጣቶችን ትኩረት ያደረገ ሲሆን የተባበሩት መንግስታትን የ2030 አጀንዳና የፓሪሱን የያየር ንብረት ለውጥ ውሳኔዎችን ዕውቅና ሰቷል።

አዲሱ የአፍሪቃና የአውሮጳ ህብረት አጋርነት አቅጣጫ

የትብብሩን ሂደት  የሚፈታተኑ ክስተቶች  

ከዚያ በኋላ ኮቪድን ተክትሎ ዳግም በብራስልስ በየካቲቲ 2022 የተከሂደው ጉባኤ ለሰላምና ለዘላቂ የኢኮኖሚ እድገት በጋራና በትብብር ለመስራት ዳግም ቃል የተገባ ቢህንም፤ ከዚያ ግዜ በሁላ ግን በተለይም የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት መጀመርን ትከትሎ ግንኑነቱ በነበረበት ስሜትና ፍጥነት እየሄ ነው ማለት እንደሚያስቸግር ነው የሚታወቀው።ምንም እንኳ  ጦርነቱ በሩሲያና ዩክሬን መካከል ቢሆንም የአውሮፓ ህብረት በቀጥታም ባይሆን ከዩክሬን ጎን ተስልፎ በሩሲያ ላይ የኢኮኖሚና የዲሎማሲ  እርምጃዎችን በመውሰድ መሆኑ ይታወቃል። ሩሲያ የምታካሂደው ጦርነት አለማቀፍ ህግን የጣሰና ያገሮችን ሉላዊነት የደፈረ ነው በማለትም አለማቀፉ ማህብረሰብ በተለይም አጋር የሆነው አፍሪካ ሩሲያን በማውገዝ ከዩክሬንና ክህብረቱ ጎን ሊቆሙ እንደሚገባ ያውሮፓ ህብረት በግልጽ ሲጠይቅና ሲያሳስብ ቆይቷል። ሆኖም ግን በዚህ በኩል ህብረቱ አፍሪካን በጠበቀው ልክ እንዳላገኘውና በዚህና ብሌሎችም ምክኒያቶች አጋርነቱና ትብብሩ ወደ ላቀ ድረጃ ሳይሸጋገር ቆይቷል። 

ከዚያ በኋላ ኮቪድን ተክትሎ ዳግም በብራስልስ በየካቲቲ 2022 የተከሂደው ጉባኤ ለሰላምና ለዘላቂ የኢኮኖሚ እድገት በጋራና በትብብር ለመስራት ዳግም ቃል የተገባ ቢህንም፤ ከዚያ ግዜ በሁላ ግን በተለይም የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት መጀመርን ትከትሎ ግንኑነቱ በነበረበት ስሜትና ፍጥነት እየሄ ነው ማለት እንደሚያስቸግር ነው የሚታወቀው።ምስል፦ DW/G. Tedla

ትብብሩን አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች   

ሆኖም ግን ባለፈው ዕሮብ  የህብረቱና የአፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ተሰብሰበው የትብብሩን ሂደትና ውጤት በመገምገም ተጠናክሮ ለመቀጠል የሚያስችሉ ውሳኔዎችንና መግለጫዎችን በማውጣት ለሰባተኛው የመሪዎች ጉባኤ ዝግጅት መጀመሩን አስታውቀዋል ።

ያውሮፓ ህብረት የውጭ ግንኙነት ሀላፊና የስብሰባው መሪ ወይዘሮ ካያ ካላስ በሰጡት መግለጫ የስብሰባው ስፋትና የነበረው ተሳትፎ  የትብብሩን ህያውነት ብቻ ሳይሆን ጥንካሬውንም የሚያመላክት  መሆኑን ገለሰዋል፤ “ የአውሮፓ ህብረትና ያፍርካ ትብብር ባለፉት ሀያ አምስት ዓመታት በርካታ ውጤቶችን አስገኝቷል።  በዚህ ጉባኤ ከሰባ በላይ ሉኡካንና ካምሳ በላይ ሚኒአትሮች መገኘታቸው  በራሱ ትብብሩ ምን ያህል ትልቅና አስተማማኝ መሆኑን ያሚያሳይ ነው” በማለት ይህም በዚህ አመት መጨረሻ የሚካሄደው ጉባኤ የተሳካ እንደሚሆን የሚያሳይ መሆኑን አስታውቀዋል።ሰባተኛው የሁለቱ አህጉሮች የመሪዎች ጉባኤ መቼና የት የት እንደሚካሄድ  በትክክል አይገለጽ እንጂ በዚህ በያዝነው ያአውሮፓውያኑ አመት መጨረሽ  በአፍሪካ አንደኛው አገር እንደሚሆን ታውቋል።

የአውሮጳ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት የኢትዮጵያ ጉብኝት 

ትብብሩ የተመሰረተባቸው መርሆዎች   

ትብብሩ ተመሰረተባቸው የሚባሉት አራት ምሰሶዎች  ብልጽግና፣ ሰላም፤ የሰው ሀይል እድገትና የባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ እንደሆኑ ይገለጻል። ብልጽግና ሲባል በዘላቂ የኢኮኖሚ እድገት ህዝቦችን አካባቢዎችንና ድርጅቶችን ማገኛነት ሲሆን፤ በተለይም የየር ንብረት ለውጥን ለመቁቋም የሚረዱ ኢንቨስትሜንቶችንና የመሰረተ ልማት ግንባታ ልማቶችን  የመሳሰሉ ፕርግርሞችን የሚያካትት ነው።  በዚህ በኩል ያለውንና  ህብረቱ ለአፍሪካ ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ የሚያፈስ መሆኑን ወይዘሮ ካያ ቦሶስተኛው የሁለቱ አህጉሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ አንስተዋል፤ “ ያውርፓ ህብረትና አባል አገሮች ላፍሪካ ዋናዎቹ አጋሮች መሆናቸው የታወቀ ሲሆን ለየር ንብረት ለውጥ መቋቋሚያ፤ ለመሰረተ ልማት ግንባታና ሌሎች አስፍላጊ ልማቶች የሚሆን 150 ቢሊዮን ኢሮ ኢንቨስት ለማድረግ ወስኗል” በማለት አውሮፓ ለትብብሩ ያለውን ፍላጎትና ቁርጠኘት አስገንዝበዋል።

ውይዘሮ ካያ አክለውም ያውርፓ ህብረት አፍሪካ በአለማቀፍ መድረኮች ተገቢው ውክልና እንዲኖረውና ድምጹ እንዲሰማ ብሎም ለአዲስ አለማቀፍዊ ስራት ግንባታ የራሱን አስተዋጾ እንዲያደርግ ህብረቱ በግምባር ቀደምትነት ሲታገል የቆየና የሚታገልም መሆኑንም አስታውቀዋል። “ ያውርፓ ህብረት አፍሪካ በባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ተገቢው ቦታ  እንዲኖረው ጥረት ይደርጋል።  በሀያዎቹ  በማደግ ላይ ባሉ አገሮች ቡድን ውክልና እንዲኖረው ትልቅ ዘመነ ያደረግነው እኛ ነብርን በማለት በመንግስታቱ ድርጅት የሁለቱ ማለት ያፍርካና የአውሮፓ ህብረት  ውክልና አርባ  ከመቶ መሆኑ ደግሞ  የድርጅቱንም ደንብና አሰራር ለማሻሻል የሚያስችል አቅም ያሚያስገኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የአውሮጳ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ 

ትብብሩን የሚፈታተኑ ተግዳሮቶች

ይሁን እንጂ ባሁኑ ወቅት በዓለም ላይ የተፈጠረው ቀውስና የጂኦፖለቲካ ውጥረት የአህጎሮቹን ግንኙነት ቢያንስ በተመሰረተብቸው መርሆች እንደነበረ እንዳይቀጥል ተግዳሮት እየሆነበት እንደሆነ ነው የሚታመነው ።  የአህጉሮቹ ትኩረቶችና ፍላጎቶች እየተራራቁና አንድንዴም እየተጋጩ መሄዳቸው ፤አባል አገሮች ህብረቱ አራምዳቸዋለሁ ከሚላቸው እሴቶቹ ይልቅ በውስጥ የፖለቲካ አጅንዳዎች የሚመሩና የሚዘወሩ መሆኑ፤ ግንኙነቱ በተፈለገውና በመርሆዎቹ መሰረት እንዳይቀጥል  አድርጎታልም እየተባለ ነው። ለምሳሌ ዛሬ በአውሮፓ በዋናነት የስደተኖች ችግር የሚቀነቀን ሲሆን አንዳንድ አባል አገሮች ከህብረቱ እሴቶችና ከትብብር ስምምነቱ ውጭም ቢሆን ካፍርካ አገሮች ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት በማድረግ ሰዎችን አስገድዶ ለመመለስ የሚያደርጉት ጥረት የግንኙነትና ትብብር መርሆዎችን ብቻ ሳይሆን አለማቀፍ የሰባዊ መብት ድንጋጌዎችን ጭምር የሚጥስ መሆኑን የሰባዊ መብት ድርጅቶች ይገልጻሉ።

ይሁን እንጂ ባሁኑ ወቅት በዓለም ላይ የተፈጠረው ቀውስና የጂኦፖለቲካ ውጥረት የአህጎሮቹን ግንኙነት ቢያንስ በተመሰረተብቸው መርሆች እንደነበረ እንዳይቀጥል ተግዳሮት እየሆነበት እንደሆነ ነው የሚታመነው ።ምስል፦ Nicolas Tucat/AFP

 

 በዩክሬንና ሩሲያ መካከል የሚካሄደው ጦርነትና የአውሮፓና አፍርካ አቋም መለያየት አንዱ  በሁለቱ ትብብር ላይ አሉታዊ ተጽኖ ያሳደረ ክስተት እንደሆነም ይነገራል።  አውሮፓ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የከፍተችው ጦርነት ያለማቀፍ ህግንና የሁቱንም ወገንቾ የትብብር መርሆችንና እሴቶች የሚጥስ በመሆኑ እንዲወገዝና አፍርካ ከዩክሬንና ያውሮፓ ህብረት ጎን እንዲሰለፍ ይፈልጋል። አፍርካ ግን ጦርነቱ በሰላምና ድርድር እንዲፈታ ከመጠይቅ ውጭ አቋም ወስዶ ካንዱ ወገን  ሲቆም አልታየም። ይልቁንም ህብረቱና ሌሎችች ምራባውያን በሩሲያ ላይ የሚያስተላልፏቸውን ማእቅቦችና የፖለቲካ ውሳኔዎች ተግባራዊ ባለማድረግ ሩሲያ እንዳትገለል አስተዋኦ በማድረግ ይከሰሳል ።

የአውሮጳ ህብረት የስደት ፖሊሲ እና ትችቱ 

ሊሎች በግንኙነቱ ላይ የሚታዩ እጸጾች

 በሌላ በኩል አውሮፓ ለአፍርካ ችግሮች ተገቢውን ትኩረት  ባለመስጠትና ለመርሆዎችና እሴቶቹ ታማኝ ባለመሆንም በስፊው ይወቀሳል። ለምሳሌ በሱዳንና ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ እየተካሄዱ ባሉ ደም አፋሳሺ ጦርነቶች የሚደርሱት ሰባዊ ቀውሶች ከፍተኛ ሆነው ሳላ፤ ጦርነቱን ለማስቆምም ሆነ ሰባዊ እርዳታ ለማድረስ የሚደረገው ጥረት ከሚጠበቀው በታች ነው በማለት  አውሮፓውያኖቹ  በአፍርካ ላሉ ችግሮች እኩልና ሚዛናዊ አመለካከት የላቸውም በማለት የሚከሱ አሉ። ፡በአፍርካና አውሮፓ ግንኑነት ላይ የሚሰራው የአውሮፓ የዕድገት ማዕከል  በእንግሊዝኝ ምህሳሩ ( Ecdpm) የተሰኘው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ከፍተኛ ባለሙያ  የሆኑት ወይዘሮ ካትሊን ቫን ሆፍ ይኸው ስሜት መኖሩን ነው የሚገልጹት፤ “ ባፍሪካውያኑ በኩል በዕክሉነት እንደማይታዩና አውሮፓውያኑ ወጥ አመላከክት እንደሚጎላቸው፤ እናምንባቸዋለን በሚሏቸው እሴቶች የማይኖሩ ናቸው” በማለት ቅሬታ የሚያሰሙ መሆኑን  ነው የሚናገሩት።

በሱዳንና ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ እየተካሄዱ ባሉ ደም አፋሳሺ ጦርነቶች የሚደርሱት ሰባዊ ቀውሶች ከፍተኛ ሆነው ሳላ፤ ጦርነቱን ለማስቆምም ሆነ ሰባዊ እርዳታ ለማድረስ የሚደረገው ጥረት ከሚጠበቀው በታች ነው በማለት  አውሮፓውያኖቹ  በአፍርካ ላሉ ችግሮች እኩልና ሚዛናዊ አመለካከት የላቸውም በማለት የሚከሱ አሉምስል፦ picture-alliance/AA/Palestinian Prime Ministry Office

 

ፕሬዝዳንት ትራም የሜክተሉት ያሜርካ ትቅደም ፖኢሲም አውሮፓን በብዙ መልኩ ያጋለጠውና ከአፍሪካና ሌሎች አገሮች ጋር የመሰረታቸው ግንኙነቶችና ትብብሮችም የሚያቃውስ ሁኗል።  በዩክረን ላይ በወሰዱት አቋምና በአውሮፓ ጭምር ከፍቱት የንግድ ጦርነት ምክኒያት አውሮፓ ወደ መክላከያ ግንባታ የገባ በመሆኑ በብዙዎቹ የህብረቱ አባል አገሮች የልማትና የትብብር በጅቶች  መቀነስ ወይም መታጠፍ እየታየ ሲሆን ይህም በአለማቀፍ የርዳታና ትብብር ፕሮግራሞች ላይ አሉታዊ ተጽኖ እንዳያሳድር አስግቷል።

የአውሮጳ ህብረት አዲሱ የልማት መርህ መመሪያ

ትብብሩ በቀጣይ ወዴት?

ሆኖም ግን አውሮፓ አፍርካን ሊያጣው የማይፈልግ ተፈጥሩዊ አጋሩና ጠቃሚው እንደሆነ በማሰብ ትብብር አጋርነቱን ወቅቱ በሚጠይቀው ሁኔታ በማሻሻል  አጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው የሚታማነው። ቻይናና ሩሲያ በአፍርካ ያላቸው ሚናና እያደገ የሄደው ተቀብይነታቸው  አውሮፓ በጓሮው ያለውን ገበያና ጥሬ ህብት እንዳያጣ የሚያሰጋው ሲሆን፤ ለዚህም ትብብር ግንኙነቱን አጠናክሮ ከመቀጠል ውጭ አማራጭ እንደለሌለው የሚናገሩት ተንታ\ኞች፤  መጭው የመሪዎች ጉባኤ እነዚህ ሁኔታዎች በማጤን ትብብሩን የበለጠ እኩል ተጠቃሚ በሚያደርጉ መርሆዎች ላይ በመመስረት እንደሚያስቀጥሉት ያላቸውን  እምነት ይገልጻሉ።

ገበያው ንጉሴ

ታምራት ዲንሳ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW