ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በዓለም መሪዎች ሲታወሱ
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 15 2017
ፖፕ ፍራንሲስ በዓለም መሪዎች ሲታወሱ
ባለፈው ሰኞ የፋሲካ ማግስት የሮማው ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ በ88 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውን ተክትሎ የበርካታ አገሮችና የአለምቀፍ ድርጅቶች መሪዎች ሀዘናቸውን እየገለጹ ናቸው። የላቲን አሜሪካዋ አርጀንቲና ተወላጅ የሆኑት ፖፐ ፍራንሲስ ከደቡባዊው የዓለማችን ክፍል የወጡ የመጀመሪያው የአለም ካቶሊክ ቢተክርሲቲያን መሪ ነበሩ። ጳጳሱ በካቶሊክ ቢተክስርቲያን ለውጥ ያመጡ፣ ክድሆችና ከተገፉ ህዝቦች ጎን በመቆም የሚታውቁ፤ ለሰላም የሚሟገቱና የሚጮሁ እውነተኛ የድሆችና ጭቁኖች ጠበቃ ስለመሆናቸው ብዙ ተብሎላቸዋል፤ እየተባለላቸውም ነው ነው።
የመሪዎች የሀዘን መግለጫና መልዕክት
ዜና እረፍታቸው እንደተሰማም ብዙዎቹ የዓለም መሪዎች ስለጳጳሱ መልካም ተግባር በማውሳት በሞታቸው የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።የአውሮፓ ህብረትና ኮሚሽን ፕሬዝዳንቶች በየግላቸው ቀድመው ባሰታላለፏቸው መልክቶች ፖፐ ፍራንሲስ አስተማሪነታቸውና አራያነታቸው ለካቶሊክ እመንት ተክታዮች ብቻ ሳሆን በሚሊዮን ለሚቆጠሩ የሌሎ እምነቶች ተከታዮችም ጭምር ነበር በማለት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል። የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስተር ጆርጂያ ሜሎኒ ደግሞ እሳቸው ትልቅ እረኛ ነበሩ በማለት በግላቸው አስተማሪያቸውና መካሪያቸው እንድነበሩ በሀዘን መግለጫቸው ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንት ትሩምት ትናንት ከኋይት ሀውስ በሰጡት መግለጫም የፖፐ ፍራንሲሲን መልካም ሰውነትን አውስተው ለክብራቸው በመላ አሜሪክ ባንዲራ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ ያዘዙ መሆኑን አስታውቀዋል፤ “ ለሳቸው ክብር የአሜሪካና የፌዴራል ግዝቶች ባንዲራዎች ጭምር ዝቅ ብለው እንዲውለበልቡ አዝዣለሁ” በማለት መልካም ሰውና አለምን የሚወዱ ታትሪ ሰው የነበሩ መሆኑን ገልጸዋል።
የብራታኒያ ጠቅላይ ሚኒስተር ኪር ስታርመር ባወጡት መግለጫም ፖፕ ፍርናሲስን “የድሆችና የተገፉ ህዝቦች ጳጳስ ነበሩ” በማለት የተሻለ አለም እኒዲፈጠር የሚጥሩና ተስፋም የሚያደርጉ ነበሩ ሲሉ ገልጸዋቸዋል።
ዋና ጸሀፊ ጉቴረሽና ሌሎች ስለ ፓፓው
የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንንቶኒዮ ጉቴረሽም የፖፕ ፍርንሲስ ሞት ሀዘን ለካቶሊኮች ብቻ ሳይሆን በምግባራቸውና በትምህርታቸው በአራያነት ለሚከተሏቸው ሁሉ መሆኑን በመግለጽ ትተውት ያለፉትን ውርስ አውስተዋል፤ “ የእምነትን የአግልግሎትን፤ ለሁሉም በተለይም ለተገለሉና በጦርነት ውስጥ ለሚሰቃዩ ፍቅርንና አጋርነትን የማሳየትን አስፈላጊነት ትተው አልፈዋል” ብለዋል።
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ባስተላለፉት መልክትም ፖፐ ፍራንሲስ ለካቶሊሊክ ቤተክርስቲያን ምእመናን ብቻ ሳይሆን ለዓለም ባጠቃላይ ትልቅ ስራ የሰሩ መሆኑን በመግለጽ ህዘናቸውን ለመላ ክርስቲያኖች በተለይም ለካቶሊኮች አስተላልፈዋል።
በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ ህልፈት የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን አስተያየት
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ፤ ፖፕ ፍራንሲስን “ሁላችንንም ጥሩ ላማድረግ የሞከሩ የተለዩ መሪ ነበሩ” ሲሉ ገልጸዋቸዋል ባወጡት መግለጫ።
የጀርመኑ ቻንስለር ሹልዝ በኤክስ ገጻቸው በፖፐ ፍራንሲስ ሞት የካቶሊክ ቤተክርስቲያንና አለም በሙሉ የድሆች ጠበቃ፤ የሰላም ተሟጋችና ሰላም ሰባኪን አተዋል ሲሉ አስፍረዋል ።
የቱርክ፣ የእስራኤልና ፍልስጤም መሪዎችም የጳጳሱን መልካም ሰውነት በማውሳት ሀዘናቸውን ከገለጹት ያለም መሪዎች ውስጥ ናቸው። የበርካታ የእስያ፤ የላቲን አሜሪካና የአፍሪካ አገሮች መሪዎችም በጳጳሱ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል፤በመግለጽም ላይ ናቸው።
የቀብር ስነስራት
ፖፐ ፍርንሲስ 1.4 ቢሊዮ አማኞች እንዳላት ለሚነገርላት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ የሆኑት እ እ እ 2013 ነው። የቀብራቸው ስንስራት ከሰላሳ በላይ የአገር መሪዎችና በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ምዕመናን በተገኙበት በሮም የሴንት ፒተር አደባባይ በሚቀጥሚለው ቅዳሜ የሚፈጸም መሆኑ ታውቋል።
ገበያው ንጉሴ
ታምራት ዲንሳ
ነጋሽ መሐመድ