1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የአፍሪቃ ጉዞ አላማ

ሐሙስ፣ ጥር 25 2015

ፍራንሲስ ከሮም ከመነሳታቸዉ በፊት ከርዕሰ-መንበራቸዉ ቫቲካን የወጣዉ መግለጫ እንዳመለከተዉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሁለቱን በጦርነትና ግጭት ክፉኛ የተመሰቃቀሉ ሐገራትን የሚጎበኙት ለሰላምና ለሕዝብ ደሕንነት ለመጸለይ ነዉ። አንድ የሮማ ካቶሊካዊት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ደቡብ ሱዳንን ሲጎበኝ ያሁኑ የመጀመሪያዉ ይሆናል።

DR Kongo Papstmesse in Kinshasa
ምስል፦ Jerome Delay/AP Photo/picture alliance

የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ሁለት የአፍሪቃ ሐገራትን ለመጎብኘት በያዝነዉ ሳምንት ማክሰኞ ኪንሻሳ-ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ገብተዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለአምስተኛ ጊዜ ወደ አፍሪቃ ባደረጉት ጉዞ ከኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ በተጨማሪ ደቡብ ሱዳንንም ይጎበኛሉ። ፍራንሲስ ከሮም ከመነሳታቸዉ በፊት ከርዕሰ-መንበራቸዉ ቫቲካን የወጣዉ መግለጫ እንዳመለከተዉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ሁለቱን በጦርነትና ግጭት ክፉኛ የተመሰቃቀሉ ሐገራትን የሚጎበኙት ለሰላምና ለሕዝብ ደሕንነት ለመጸለይ ነዉ። አንድ የሮማ ካቶሊካዊት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ደቡብ ሱዳንን ሲጎበኝ ያሁኑ የመጀመሪያዉ ይሆናል። ለኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ደግሞ እንደ ግሪጎሪያኑ አቆጣጠር ከ1985 ወዲህ የመጀመሪያዉ ነዉ። አንድ መቶ ሚሊዮን ከሚገመተዉ ከሰፊዋ አፍሪቃዊት ሐገር ሕዝብ 40 በመቶዉ የካቶሊክ ክርስትና እምነት ተከታይ ነዉ።የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱን ጸሎትና ቡራኬ ለመቀበል ከርዕሰ ከተማይቱ ነዋሪ በተጨማሪ በብዙ ሺሕ የሚቆጠር አማኝ ከያለበት ወደ ኪንሻሳ ሲጎርፍ ነዉ የሰነበተዉ። ይህ በእንዲህ ደቡብ ሱዳን መዲና ጁባ እንዳለ ነገ አርብ የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስን ለመቀበል ከፍተኛ ዝግጅት ላይ እንደሆነች ተነግሯል። ስለ ሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የአፍሪቃ ጉብኝትን በተመለከተ የብረስልሱን ወኪላችንን አነጋግረናል። 

ገበያዉ ንጉሴ 
አዜብ ታደሰ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ 
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW