1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሰላም የራቃት የመን

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 14 2008

የየመን ተቀናቃኝ ኃይሎች የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያመቻቸዉን የሰላም ዉይይት ባለፈዉ እሁድ ያለምንም ዉጤት አብቅተዋል። ባለፈዉ ሳምንት የተካሄደዉ የሰላም ንግግር ዉጤት ባይታይበትም ቀጣይ ዉይይት ለማካሄድ ለፊታችን ጥር 5 ቀን 2008ዓ,ም ቀጠሮ ተይዟል።

Jemen Kämpfe in Taiz
ምስል picture-alliance/Anadolu Agency/A. Seddek

[No title]

This browser does not support the audio element.

በኢራን እንደሚደገፍ የሚነገርለት ሁቲ አማፅያን መሪ ግን ከወዲሁ የመንግሥታቱ ድርጅት ያሰናዳዉ ድርድር ትርጉም የለዉም በማለት ደጋፊዎቻቸዉ የመንግሥት ደጋፊ ኃይሎች ዋና ከተማ ሰንዓን እንዳይዙ እንዲከላከሉ ተማፅነዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በበኩሉ በአማፅያኑ እና በመንግሥት ኃይሎች የተጣሰዉ የተኩስ አቁም ፀንቶ እንዲከበር እየጠየቀ ነዉ። ሁቲ አማፅያኑ የተኩስ አቁሙ ታዉጆ የመንግሥት ኃይሎች ጥቃት አድርሰዉብናል እያሉ ነዉ። የሰላም ዉይይቱን መቃወም የጀመሩት በዚህ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ነዉ የተገለጸዉ። ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሜ ሰንዓ የሚገኘዉን ጋዜጠኛ ግሩም ተክለ ኃይማኖትን ስለሁኔታዉ አነጋግሬዋለሁ።

ግሩም ተክለ ኃይማኖት

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW