1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሰመርጃም - በኮሎኝ ከተማ የሬጌ ዘፈን የሙዚቃ ድግስ

ዓርብ፣ ሐምሌ 1 2003

26ኛው የሰመር ጃም የሙዚቃ ድግስ ጀርመን ውስጥ በኮሎኝ ከተማ ሲካሄድ በሺዎች የሚቆጠሩ ተመልካቾችና 37 የሙዚቃ ባንዶች ተገኝተዋል።

ምስል DW

ሰመር ጃም የተሰኘዉ የሬጌን ስልት ብቻ የሚያስኮመኩመዉ የሙዚቃ ድግስ ጀርመን ላይ በየዓመቱ ሲካሄድ ብዙ ዓመታትን አስቆጥሯል። በሰሜን አትላንቲክ የበጋ ወራት የሚቀርበዉ ይህ የሙዚቃ ድግስ ከጀርመን ብቻ ሳይሆን ከተለያዩ የአዉሮጳ ሀገራት ታዳሚዎችም አሉት። የዘንድሮዉ 26ኛው የሰመር ጃም የሙዚቃ ድግስ ጀርመን ውስጥ በኮሎኝ ከተማ ሲካሄድ በሺዎች የሚቆጠሩ ተመልካቾችና 37 የሙዚቃ ባንዶች ተገኝተዋል። በውሀ የተከበበችው ትንሽ ደሴት ላይ ተመልካቾች የተከሏቸዉ የድንኳኖችን ብዛት ለተመለከተ፤ የሀይቲ በመሬት መንቀጥቀጥ ተመትታ ህዝቧ በወቅቱ የሠፈረበትን ሁኔታ ያስታውሳል። በሙዚቃ ድግሱ ላይ ፀጉራቸው የተጥመለመለ ወይም ድሬድ ሎክ ያላቸው በደስታ ሲፍነከነኩ ነዉ የከረሙት። ለሶስት ቀናት በቆየው የሙዚቃ ዝግጅት ላይ በየቀኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ነበር የተገኙት። ከዘፋኞች ጥቂቶቹን ብጠቅስ ዘ ኮንጎስ፣ ጂሚ ክሊፍ፣ አልፋ ብሎንዲ፤ የቦብ ማርሪይ ልጅ- ዚጊ ማርሌይ ነበሩ። ከጃይማይካ፤ ከአፍሪካና ከአውሮፓ የመጡትየሙዚቃ ባንዶች፤ በተለያየ የእድሜ ክልል ውስጥ ናቸው። የዛኑም ያህል ታዳሚዉ ከህፃን እስከ አዋቂ ነበር። ስለ ዝግጅቱ የበለጠ ለማወቅ ከፈለጉ ዘገባውን ያድምጡ።

ምስል DW
ምስል DW

ልደት አበበ

ሸዋዮ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW