1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

«ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዝግጅት እና የኢትዮጵያ ተስፋ» እንወያይ

እሑድ፣ ጥቅምት 9 2018

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምርጫ ከምርጫ ውድድር ባሻገር ፤ በሀገሪቱ ግጭቶች ቆመው ዘላቂ ሰላም ሊያሰፍን የሚያስችል ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት የሚጠይቅ እንደመሆኑ መጠን የተለያዩ ፖለቲካዊ ፍላጎቶችን እና የማህበረሰብ ክፍሎችን የሚወክሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፎ ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግም ሲነገር ቆይቷል።

Äthiopien Bonga | Wahl
መራጮች በምርጫ ላይ እየተሳተፉ ምስል፦ Shewangizaw Wegayehu/DW

ሰባተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ምልከታ

This browser does not support the audio element.

 

በኢትዮጵያ በዚህ ዓመት ሰባተኛውን ሀገራዊ ምርጫ  እንደምታደርግ እና ምርጫው ፍትሃዊ ፣ ሰላማዊ ፣ ተአማኒ እና በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው  መንግስት በሃላፊነት እንደሚሰራ የኢፌድሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀስላሴ የሁለቱን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ በከፈቱበት ወቅት አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ከነበሩ ግጭቶች እና የኤኮኖሚ አለመረጋጋት በተጨማሪ  እንደምርጫ ቦርድ ባሉ የዴሞክራሲ ተቋማት ላይ በሚነሱ የነጻነት እና የገለልተኝነት ጥያቄዎች መጪው ምርጫ ምን ያህል ይሳካ ይሆን የሚሉ ጥያቄዎች ሲነሱ ይሰማሉ።

የተቃዋሚ ፓርቲዎች በሀገሪቱ ከምርጫ ህጎች ጋር ተያይዘው የሚነሱ ጉዳዮችን ጨምሮ የአንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች መታሰር ፣ የአባላት እንቅስቃሴ መገደብ ብሎም የመገናኛ ብዙኃንን በፍትሃዊነት የመጠቀም ዕድል የማጣት ችግሮች ሲያነሱ ይደመጣል።

በተለያዩ አካባቢዎች ከነበሩ ግጭቶች እና የኤኮኖሚ አለመረጋጋት በተጨማሪ  እንደምርጫ ቦርድ ባሉ የዴሞክራሲ ተቋማት ላይ በሚነሱ የነጻነት እና የገለልተኝነት ጥያቄዎች መጪው ምርጫ ምን ያህል ይሳካ ይሆን የሚሉ ጥያቄዎች ሲነሱ ይሰማሉ።ምስል፦ Damtew Tesema

 

በዚያው ልክ የአንዳንድ የተቃዋሚ ፓርቲዎች በራሳቸው በውስጣቸው በፈጠሯቸው መከፋፈል እና የምርጫ ጊዜ ሲደርስ ብቻ መከሰት በሀገሪቱ ጠንካራ ውድድር የሚጋብዝ ምርጫ እንዳይኖር የበኩላቸውን አሉታዊ አስተዋጽዖ አበርክተዋል ፤ የሚል ትችት ሲቀርብባቸው ይሰማል። 

በምርጫው ላይ ለመሳተፍ አስቻይ ሁኔታ መኖር አለበት ምስል፦ Mulualem Tegegnework

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምርጫ ከምርጫ ውድድር ባሻገር ፤ በሀገሪቱ ግጭቶች ቆመውዘላቂ ሰላም ሊያሰፍን የሚያስችል ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት የሚጠይቅ እንደመሆኑ መጠን የተለያዩ ፖለቲካዊ  ፍላጎቶችን እና የማህበረሰብ ክፍሎችን የሚወክሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፎ ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግም ሲነገር ቆይቷል።

ኢዜማ በምርጫው ላይ ለመሳተፍ ዝግጅት እያደረገ ነው ምስል፦ Mulatu Gemechu

በኢትዮጵያ ግጭት ለቀሰቀሱ የፖለቲካ ፍላጎቶች መልስ ለመስጠት ፣ ሀገሪቱ የምትከተለው መንግስታዊ ስረዓት ብሎም ቀጣናዊ እና ዓለማቀፋዊ ሚናዋን የሚወስነው ምርጫው ዴሞክራሲያዊ ፣ ፍትሃዊ ፣ ተአማኒ እና ተቀባይነት ያለው እንዲሁም የሁሉንም የፖለቲካ ኃይሎች ተሳትፎ ባረጋገጠ መልኩ እንዲካሄድ የፖለቲካ ፓርቲዎች የውድድር ዝግጅት ወሳኝ ነው።

«ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዝግጅት እና የኢትዮጵያ ተስፋ» የሳምንቱ እንወያይ ዝግጅታችን ርዕስ ነው ።

በውይይቱ ላይ

ፕሮፌሰር ዳምጠው ተሰማ ከአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አብን ከአዲስ አበባ

አቶ ሙላቱ ገመቹ ከኦሮሞ ፍዴራሊስት ኮንግረንስ ከአዲስ አበባ

ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘ ወርቅ ከኢትዮጵያ ዜጎች ለማሕበራዊ ፍትህ ኢዜማ

ዶ/ር ራሄል ባፌ ከኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ ኢሶዴፓ ተገኝተዋል።

አዋያይ ጋዜጠኛ ታምራት ዲንሳ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW