1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሰንደቅ ዓላማ እና የሰንደቅ ዓላማ ቀን፤ የህዝብ አስተያየት

ሰኞ፣ ጥቅምት 4 2017

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ፣ የኢፌዴሪ ፕሬዘዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ እና ሌሎችም የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት በተገኙበት እለቱ በአዲስ አበባ ሲከበር “ሰንደቅ ዓላማ የነጻትና የእኩልነት ደማቅ ምልክት” ተብሏል ። ስለ ሰንደቅ ዓለማ ቀን ህዝቡ ምን ይላል?

Addis Abeba, Ethiopia
ምስል Eshete Bekele/DW

ሰንደቅ ዓላማ እና የሰንቅ ዓላማ ቀን፤ የህዝብ አስተያየት

This browser does not support the audio element.

ዛሬ የብሔራዊ የሰደቅ ዓላማ ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ17ኛ ጊዜ “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ’’ በሚል መሪ ሀሳብ ተከብሮ ውሏል፡፡

በዓሉ በፌዴራል የመንግስት ተቋማት፣ በክልሎች እና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች፣ በመከላከያ ሠራዊት ካምፖች እንዲሁም በኢትዮጵያ ኢምባሲዎች እና ሚሲዮኖች በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ዛሬ ረፋዱን 4፡3ዐ ላይ ሰንደቅ ዓላማ በመስቀል እና በሰንደቅ ዓላማ ፊት ቃለ-መሃላ በመፈፀም ነው የተከበረው።

የሰንደቅ ዓላማችን ጉዳይ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አቶ ታገሰ ጫፎ፣ የኢፌዴሪ ፕሬዘዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ እና ሌሎችም የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት በተገኙበት እለቱ በአዲስ አበባ ሲከበር “ሰንደቅ ዓላማ የነጻትና የእኩልነት ደማቅ ምልክት” ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትን ለመደገፍ በተካሄደ ሰልፍ ላይ አንድ ሰው የኢትዮጵያን ባንዲራ ሲያውለበልብምስል AMANUEL SILESHI AFP via Getty Images

በዚህን ወቅት በሀገሪቱ የሚገኙ የፖለቲካ ኃይሎች ልዩነታቸውን ተቀራርበው እንዲፈቱ ጥሪም ቀርቦ፤ ብሔራዊ አንድነት እና ሉዓላዊነት በማስከበር ኢትዮጵያን በሁሉም ዘርፍ ከፍ ማድረግ ከሁሉም የሚጠበቅ ተብሏል።የሰንደቅ ዓላማ ፉክክር የወለደው የአዲስ አበባ ውጥረት 

ለመሆኑ ስለ ሰንደቅ ዓለማና ስለ ሰንደቅ ዓላማ ቀን ህዝቡ ምን ይላል? የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ስዩም ጌቱ የህዝብ አስተያየት አሰባስቧል፡፡

ስዩም ጌቱ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW