ሰዉ ሠራሽ ማዳበሪያ
ማክሰኞ፣ መስከረም 15 2005ማስታወቂያ
የማዳበሪያ ዓይነቶችን በሁለት ከፍሎ ማየት እንደሚቻል፤ በአጠቃቀም ረገድ ደግሞ ተገቢዉን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ባለሙያዎች ይገልፃሉ።
ስለማዳበሪያ ሲነገር በቀጥታ የሚገናኘዉ ከመሬት ለምነትና በቂ ምርት ከማስገኘት አቅም ጋ ነዉ። አንዳንድ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ላለፉት ሺ ዓመታት ይህ ጉዳይ አርሶ አደሮችን ሲያሳስብ ቆይቷል፤ አሁንም በተለይ የህዝብ ቁጥር እያደገ ከመሄዱ ጋ በተገናኘ ደግሞ አሳሳቢነቱ ከፍ ብሏል።
ዘመናዊዉ ሳይንስ በ19ኛዉ ክፍለ ዘመን አጋማሽ የተጀመሩ ጥረቶች ዛሬ በተለያየ መልኩ የሚመረቱ የማዳበሪያ ዓይነቶችን አስገኝቷል። የመጀመሪያዉ በኖርዌይ እንዱስትሪ ከናይትሮጅን የተቀመመ መሆኑን ነዉ መረጃዎች የሚያመለክቱት።
ሸዋዬ ለገሠ
ሂሩት መለሰ