ሰይፍ አል ኢስላም እና የሄጉ ፍርድ ቤት17 ጥቅምት 2004ዓርብ፣ ጥቅምት 17 2004ባለፈው ሳምንት የተገደሉት የቀድሞው የሊቢያ መሪ የሞአመር ጋዳፊ ልጅ ሰይፍይ አልኢስላም ጋዳፊ ፣ ለሄጉ ዓለም ዓቀፍ የጦር ወንጀለኞች ፍርድቤት እጃቸውን ለመስጠት እንደሚፈልጉ አንድ የሊቢያ የሽግግር ምክር ቤት ባለስልጣን አስታወቁ ።ማገናኛዉን ኮፒ አድርግሰይፍ አል ኢስላምምስል dapdማስታወቂያ ስማቸው ያልተጠቀሰው እኙሁ ባለስልጣን ሰይፍ አል ኢስላም ከተጠለሉበት በረሃ ወደ ሄግ ኔዘርላንድስ የሚወስዳቸው አውሮፕላን እንዲዘጋጅላቸው እንደሚፈልጉ ተናግረዋል ። ፍርድቤቱ በበኩሉ ሳይፍ አል ኢስላም ያሉበትን ቦታና ሃሳባቸውን ለማወቅና ለማጣራት በሞመከር ላይ መሆኑን አስታውቋል ። ሂሩት መለሰ ነጋሽ መሐመድ