1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሱዳንን ለማዳን የቀረበ ጥሪ በዓለም የጤና ድርጅት

ማክሰኞ፣ ጳጉሜን 5 2016

ዓለም በሱዳን እየተካሄደ ባለው የርስ በርስ ጦርነት ምክንያት እየደረሰ ያለውን የሰው ልጅ ሰቆቃ፤ እልቂትና ስደት፤ ያገር ውድመትና ጥፋት ዐይኑን ገልጦ እንዲያይና እንዲታደግ አሁንም ጥሪ ቀርቦለታል።

ባለፈው ቅዳሜና እሁድ በሱዳን ተገኝተው የነበሩት የዓለም የጤና ድርጅት ኃላፊ ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም በአገሪቱ ግዜያዊ ዋና ከተማ ፖርት ሱዳን መግለጫ ሰጥተዋል
ባለፈው ቅዳሜና እሁድ በሱዳን ተገኝተው የነበሩት የዓለም የጤና ድርጅት ኃላፊ ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም በአገሪቱ ግዜያዊ ዋና ከተማ ፖርት ሱዳን መግለጫ ሰጥተዋልምስል -/AFP

ለሱዳን ሰላም አስከባሪ ኃይል ስለማስገባት ጉዳይ የባለሞያዎች አስተያየት

This browser does not support the audio element.

ዓለም በሱዳን እየተካሄደ ባለው የርስ በርስ ጦርነት ምክንያት እየደረሰ ያለውን የሰው ልጅ ሰቆቃ፤ እልቂትና ስደት፤ ያገር ውድመትና ጥፋት ዐይኑን ገልጦ እንዲያይና እንዲታደግ አሁንም ጥሪ ቀርቦለታል። ባለፈው ዓመት በሚያዚያ  ወር በሁለቱ የሱዳን ጦር ኃይሎች አዛዦች መካከል የተጀመረው ጦርነት ትልቋን አገር ሱዳንን አፍርሶ፤ ሕዝቧን ታይቶ ለማይታወቅ ችግር መዳረጉ የታወቀ ቢሆንም፤ ዓለም ግን እስካሁንም ተገቢውን ትኩረት እንዳልስጠው ነው የሚነገረውና የሚታመነው። 

የዓም የጤና ድርጅት ኃላፊ ጥሪ

ባለፈው ቅዳሜና እሁድ በሱዳን ተገኝተው የነበሩት የዓለም የጤና ድርጅት ኃላፊ ዶክተር ቴድሮስ አድሀኖም በአገሪቱ ግዜያዊ ዋና ከተማ ፖርት ሱዳን በሰጡት መግለጫ፤ በሱዳን ያለው ረሐብ፤ በሽታና ሞት፤ መፈናቀልና ስደት በየትኛውም የዓለም ክፍል ከሚታየው የበለጠ አስከፊ መሆኑን በማውሳት፤ ዓለም በዚህ የሱዳን ሕዝብ ሰቆቃ ላይ ዝምታውን እንዲሰብርና የበኩልን እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል። "ሱዳናውያን በክፍተኛ የችግር ማዕበል እየተሰቃዩ ነው። ሱዳን በዓለም ከፍተኛው የህዝቦች መፈናቀል የታየበት ነው። በርሀብ የሚሞተው ህዝብ ብዛት እየጨመረ ሲሆን፤ ከሱዳን ሕዝብ ግማሽ የሚሆነው 25.6 ሚሊዮን ሕዝብ ለስደትና መፈናቀል ተዳርጓል” በማለት አለም ሱዳንን ከፍጹም ውድመትና ህዝቧንም ከጥፋት ለመታደግ እንዲነሳ ጥሪ አቅርበዋል።

በሱዳን የሰላም አስከባሪ ኃይል እንዲመደብ የቀረበው ሐሳብና የተፋላሚማዎቹ ኃይሎች ምላሽ

ባለፈው አርብም ካንድ አመት በፊት በስዳን የሚፈጸመውን የሰባዊ መብት ጥሰት እንዲያጣራ በመንግንስታቱ ድርጅት የተቋቋመው የባለሙያዎች ቡድን በሰጠው መግለጫ፤ የቡድኑ የምርመራ ግኝት በሱዳን  ያለው ሁኔታ የሰላም አስከባሪ ኃይል እንዲገባ የሚጠይቅ መሆኑን አስታውቋል።  የኮሚቴው ሰብሳቢ ሚስተር  ሞሃምድ ቻንዴ ኦትማን የሰላም ስከባሪ ሀይል አስፈላጊ የሆነበትን ምክኒያት ሲያብራሩ፤ ” ሁለቱም ተፋላሚ ወገኖች የሰላማዊ ሰዎችን ደህንነት የሚያስጠብቁ አለመሆናቸውን በምርመራችን አረጋግጠናል። ይልቁንም በክፍተኛ የሰባዊ መብት ጥሰት የተዘፈቁ በመሆናቸው የሰላማዊ ሰዎችን ከጥቃት ለመከላከል  የውጭ ኃይል ባፋጣኝ መግባት ይኖርበታል በማለት ኮሚቲያቸው በሱዳን ነጻና ገለልተኛ የሰላም አስከባሪ ኃይል  እንዲመደብ ምክረ ሀሳብ ያቀረበ መሆኑን አስታውቀው ነበር።

በርስ በርስ ጦርነት በተዘፈቀችው ሱዳን የሴናር ግዛትምስል Ozge Elif Kizil/AA/picture alliance

የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች  ግን ይህንን የሰላም አስከባሪ ሀይልን አስፈላጊነት አስልተቀበሉትም። በተለይ ከጄንራል አልቡርሀን ጋር የሚሰራው የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ባወጣው መግለጫ፤  የመንግስታቱ ድርጅት የሰላም አስከባሪ ሀይል ሀሳብን ሱዳን የማትቀበል መሆኑን በመግለጽ፤ የኮሚቴው ህላፊነትና ተግብርም ይህን ጥይቄ ወይም ምክረሀስብ ማቅረብ አለመሆኑን አስታውቋል።

በሰላም አስከባሪ ኃይል ላይ የባለሞያዎች አስተያየት

የመንግስታቱ ድርጅት የሰላም ስከባሪ ኃይል ሀሳብ ግን በፖለቲካ ተንታኖችና ታዝቢዎችም ጥያቄ ይቀርብበታል።፡ ሮናልድ ማርቻት የተባሉ የአፍርካ ቀንድ ተንታኝ፤ " ባለው ሁኔታ የውጭ የሰላም አስከባሪ ሀይል ቢገባ፤ ጊዜውን፤ ሀዝቡን ክመጠበቅ ይልቅ እራሱን ከጥቃት በመከላከል የሚያሳልፍ ነው የሚሆነው” በማለት የሰላም ስከባሪ ሀይል የታለመትን ስራ እንዲሰራ መሟላት ያለባቸው ነገሮች እንዳሉና እነዚህ ሁኒታዎች ግን  በሱዳን እንደሌሉ ተናግረዋል።

ከአፍሪቃ ሴኩሪቲ ጥናት ማዕከል ዶክተር ዎሌ ኦጄዋሌም፤  በአፍሪቃ የሰላም አስከባሪ ኃይል ተመክሮ የታየው ግጭቶችን ሲያሲያስወግድ ሳይሆን ሲያራዝም ነው በማለት  ለሱዳን የታሰበው የሰላም አስክባሪ ሀይልም የችግሩ አካል ላለመሆኑ ዋስትና እንደሌለ በመግለጽ ጉዳዩን በጥንቃቄ ማየት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።” ጉዳዩን በጥንቃቄ ማየት ይኖርብናል። ምክኒያቱም በኮንጎ፣ ማሊና ሌሎች ያፍርካ አገሮች የተመደቡት የስላም አስከባሪ ሀይሎች የተደበላለቀ ስሜት ነው ያሳደሩት። በመሆኑም በሱዳንም የስላማ ስከባሪ ኃይል ማስፈሩ ምናልባትም ችሩን የበለጠ ሊያወሳስበው ይችላል” በማለት  ሀሳቡን እሳቸውም እንደማይቀበሉት ገልጸዋል።

የርስ በርስ ግጭት ያዳቀቃት ሱዳን ዖምዱርማን ከተማምስል Mudathir Hameed/dpa/picture alliance

ባለሙያዎቹ የሚሉት ከስላም አስከባሪ ኃይል ይልቅ በቅድሚያ ሁለቱን ተፋላሚ ወገኖች ለውይይትና ድርድር ማቀራረብ ይስፈልጋል ነው። ሁለቱም የሱዳን ተፋላሚዎች  ያለውጭ ድጋፍና አይዞህ ባይነት ጦርነቱን ማካሄድ አይችሉም የሚሉት እነዚህ ታዛቢዎች፤ ከቅርብም ሆነ ከሩቅ  ላንዳቸው ወይም ለሁለቱም ተፋላሚ ወገኖች እርዳታ የሚያደርጉ መንግስታት፤ ይልቁንም በነዚህ ሀይሎች ላይ ተጽኖ በመፍጠር ለድርድርና ውይይት እንዲቀመጡና አገራቸውን በራሳቸው ካማጥፋት እንዲቆጠቡ ማድረግ ያስፈልጋል ባይ ናቸው።

ገበያው ንጉሤ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW