ሱዳን ወታደራዊ መንግሥትና የተቃዋሚዎች ስምምነት
ሰኞ፣ ሐምሌ 1 2011ማስታወቂያ
ሥልጣን ይዞ የሚገኘዉ የሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤት እና የተቃዉሞ እንቅስቃሴ መሪዎች ሀገሪቱን በጋራ ለማስተዳደር መዲና ኻርቱም ከሥምምነት መድረሳቸው ለሱዳን አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ከፍቷል። ዛሬ የመግባብያ ሰነዳቸዉን እንደሚጠበቀዉ ሁለቱ ወገኖች በስምምነታቸዉ መሠረት ሀገሪቱ በምትመርጠዉ ምክር ቤት ሲቪልና የጦር መኮንኖቹ በጋራና በፈረቃ እየተቀባበሉ ይመራሉ። ይህን ሦስት ዓመት የሚቆየዉን አካል አንዳንዶች የሽግግር መንግሥት ሲሉት ሌሎች በበኩላቸዉ የጣምራ መንግሥት ብለዉታል። ከስምምነቱ መድረስ የቻሉት በአፍሪቃ ሕብረት እና በኢትዮጵያ አሸማጋይነት መሆኑ ቢነገርም፤ ውስጥ አዋቂ ምንጮች የዩናይትድ ስቴትስ እና የአረብ ሃገራት ተፅዕኖ ማድረጋቸውን ለዜና አውታሮች ገልጸዋል።
ይልማ ኃይለሚካኤል
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ