1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ሱዳን ውስጥ እስካሁን የተሳሳተ መረጃ ሲሰጡ ቆይተው ኣሁን ሰዎች ሞተውብናል

ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 10 2012

የኮሮና ቫይረስ በቻይናዋ ውሐን ከተማ ከተከሰተ ጀምሮ ከሩቅ እንከላከለዋለን እያሉ ሲፎክሩ የነበሩትን ሀያላን ሐገሮች አሜሪካንን ጭምር እየፈተነ ያለ አደገኛ ተህዋሲ እንደሆነ ማንኛውም ሰው የሚረዳው ሐቅ ነው።

የአድማጮች ማህደር

This browser does not support the audio element.

ጤና ይስጥልኝ የዝግጅታችን ተከታታዮች፤ የዛሬውን የአድማጮች ማህደር ዝግጅት የምንጀምረው፤ አለማየሁ መላከ ( መላኩ) የተባሉት የዝግጅታችን ተከታታይ እና ተሳታፊ በላኩልን ግጥም ይሆናል።
ግጥም
ሙዚቃ
ቀጣዩን መልዕክት የላኩልን ጥቁር አሚን ናቸው ከደሴ እሳቸውም ከከበረ ሰላምታ በኋላ
በመቀጠል ያለኝ አስተያየት ዓለምን በአጭር ጊዜ እያሽመደመደ ስላለው የኮሮና ኮቪድ 19 ኝ ይመለከታል ይላሉ።
ይሕ የኮሮና ቫይረስ በቻይናዋ ውሐን ከተማ ከተከሰተ ጀምሮ ከሩቅ እንከላከለዋለን እያሉ ሲፎክሩ የነበሩትን ሀያላን ሐገሮች አሜሪካንን ጭምር እየፈተነ ያለ አደገኛ ተህዋሲ እንደሆነ ማንኛውም ሰው የሚረዳው ሐቅ ነው።
ታድያ ሲሞካሹ የነበሩት ሀገራት ዛሬ መውጫ ቀዳዳ ያጡለትን ችግር የኛ ሐገር ዜጋ በኢትዮጵያ መግባቱ እየታወቀ ነገሩን አቅልሎ በማየት ማሕበረሰቡ የተዘናጋበት ሁኔታ ሊገባኝ አልቻለም። ተሕዋሲው ተሰራጭቶ እንደአሜሪካ በበሽተኛና በሞት እሰከምንጥለቀለቅ ድረስ ከሆነ የምንጠብቀው ያሳዝናል ሰው በቤትሕ ተቀመጥ ሲባል ልክ በቤትሕ እንዳትቀመጥ ውጣ የተባለ ይመስል ሁሉም በየከተማው ወጥቶ ርቀቱን ሳይጠብቅ ተዛዝሎ ወሬውን ሲሰልቅ ይውላል ያመሻል። አስቸኳይ ጊዜ አዋጅም ቢታወጅ ችግሩ ተባባሰ እንጅ አልቀነሠም። ማሕበረሰቡ መፍራት ያለበት በሽታውን እንጅ ሕጉን አልነበረም።  እኔ በምኖርበት ደሴ ከተማና ዙሪያዋ ጭምር በጫት ንግድ የተሠማሩ አካላትና የቃሚው ማሕበረሰብ ወረርሽኙን ያባብሱታል እንጅ ጫት ሻጩም ገዥውም ፖሊሱም የአካባቢ ሚሊሻውም ጭምር በዚሕ የጫት ሱስ የተለከፉ በመሆናቸው በየስርቻው ይቃማል ይጨሳል። ታድያ ሕግ አስከባሪውም ጭምር የሱስ ተገዥ በሆነበት ሀገር እንዴት ነው ከተጋረጠብን ችግር የምንላቀቀው በሌሊት በአይሱዙ የጭነት መኪና ከአንዱ ወረዳ ወደሌላኛው ወረዳ  እንደልብ እየተዘዋወረ ምግብ አደላ ነው ወይስ ዕፅ? ታድያ ይሕን ችግር የሚገታው ማነው ?
ሌላው የአምልኮ ቦታወች መቸ ሰው በብዛት ተሰባስቦ ማምለኩን ተወና ክልከላው አቢያተ ክርስቲያንን አያካትትም ከሆነ አላቅም እናም እባካችሁ ሳይቃጠል በቅጠል ነውና ቢታሰብበት መልካም ነው እላለሁ የናንተው 
ጥቁር አሚን ከ ደሴ ✍
ከጫት ጋር በተያያዘ አንድ በድምፅ የደረሰንም አስተያየት አለ። 
ሰለሞን ማሞ ደግሞ ከወረባቦ አንድ ግጥም ልከዋል። ርዕሱ አዋጁ ምን ይላል ይሰኛል።
ቀጣዩ የፁሁፍ መልዕክት ደግሞ የደረሰን ከሱዳን በቴሌግራም ነው፤ 
ጸሀፊውበኣገራችን ሙቀት ስላለ ቫይረሱ ሙቀት ኣይችልም እያሉ ሱዳን ውስጥ እስካሁን የተሳሳተ መረጃ ሲሰጡ ቆይተው ኣሁን ሰዎች ሞተውብናል ከ 30 በላይ በበሽታው ተይዘዋል ለ21 ቀን ከቅዳሜ ጀምሮ ከቤት እንዳትወጡ ተብለናል። በጣም ያሳዝናል ብዙ ኢትዮጵያውያን በሚኖሩባት ካርቱም ኣሁንም ስጋት ውስጥ ገብተናል። 
በማለት ፀሀፊው ዶይቸ ቬለ በበቂ ሁኔታ ሱዳን ላይ እየሆነ ስላለው ነገር አልዘገበም ሲሉ ይወቅሳሉ።የተከበሩ የዝግጅታችን ተከታታይ ጥቆማዎንና አስተያየትዎን ተቀበልናል።እናመሰግናለን።

 ሌሎች ተከታታዮቻችንም ተመሳሳይ መረጃ ልከውልን ነበር። ሁላችሁንም እናመሰግናለን። አድማጮች ቴሌግራም ላይ በዶይቸ ቬለ ስም አርማውን ጨምሮ የተከፈቱ ገፆች እንዳሉ በደረሰን ጥቆማ መሠረት ለሚመለከተው አካል አመልክተናል። ርምጃ እስከሚወሰድ ድረስ በምታገኟቸው መረጃዎች ግራ እንዳትጋቡ እናሳስባለን። ትክክለኛው የቴሌግራም ገፃችን 29 ሺ የሚደርሱ ተከታዮች ያሉት ነው። በስህተት ሌላ ቦታ ገብታችሁ ከሆነ አባላቱን በትክክል ተመልከቱ። ከዚህ ውጪ  @dwamharicbot የሚባል ገፅ አለን ።ይህ ገፅም  አድማጮች አስተያየት መስጠት የምትችሉበት ነው። 
እባካችሁ ትኩረት እንስጥ!! የሚሉት አስተያየት ሰጪ ደግሞ ስማቸውን አልገለፁም፤
የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እንደ ሰብዓዊ ፍጡር ያሉንን መብቶች ሁሉ እያጣን ነው! የነፃነት፥ የፍትህ፥ የትምህርት፥ የመስራት…..… መብቶቻችን ተገድበዋል። 
ይህ እየሆነ ያለው ቫይረሱ በፈጠረው አስገዳጅ ሁኔታ ክቡር የሆነውን የሰውን ልጅ ህይወት ለመታደግ ሲባል ነው። መንግስት የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ባለው አቅም እየጣረ ነው። ከባባድ እርምጃዎች እየወሰደ ነው። የእኛን በህይወት የመኖር መብት ለመጠበቅ መንግስት በተቻለ መጠን እየሰራ ነው።
እኛ ግን ጤንነቱ ወይም ህይወቱ የራሳችን መሆኑን የረሳን ይመስለኛል። በነፍሳችን እየቀለድን ነው። የድርሻችንን ሳንወጣ እጃችንን አጣጥፈን ተአምር እየጠበቅን ነው፥ እጃችንን መንግስት ላይ እየቀሰርን ነው። የራሳችንን ህይወትና ጤንነት የመጠበቅ ግዴታ ያለብን እኛ ነን። እስኪ እራሳችንን እንጠይቅ ህይወታችንና ጤናችንን ለመጠበቅ ራሳችን ምን እርምጃ ወስደናል? ምን ያህል እየጣርን ነው? ከመንግሥት ጥረት አንፃር የእኛ የባለመብቶች ሚና እና አስተዋፅኦ የቱ ጋር ነው?  እባካችሁ ለተከሰተው አስገዳጅ ሁኔታ እና እየተወሰደ ላለው እርምጃ ትርጉም እንስጥ። እናገናዝብ። ከሌሎች ሰቆቃ እንማር። በዓለም ላይ የምናየው እልቂት ፊልም አይደለም፤ መራራ እውነታ ነው! ሃላፊነት ይሰማን! ግዴታችንን እንወጣ!  ብለዋል አስተያየት ሰጪው
»»»»»»
Demelash የተባሉ አስተያየት ሰጪ ደግሞ
በዓለም አንገብጋቢ  ስለሆነው የኮሮና  COVID 19 ወረርሽኝ ኢትዮጵያ  ውስጥ በአንዳንድ  ጤና ጣቢያ ስላለው ዝግጅት ለመናገር  ለመጠየቅ እና ለማስተባበር ያክል  ነው. ይላሉ... የጤና  ባለሙያ  እንደሆኑ የገለፁልን ደመላሽ ቀጥለውም
እኛጋ ምንም  መሳሪያዎች፣ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ማስኮች የሉም። የቅድመ  መከላከል  ስራ እንዳለ ሆኖ  ከላይ እና ከታች ያሉ የጤና ኃላፊዎች ጠንካራ ስራ መስራት ይጠበቅባቸዋል። በተለይ ማስተባበር አለባቸው።  ምክንያቱም ባለሙያው ከተበከለ ሌላውን ማን ያክመዋል?  የዘውትር የቴሌግራም ተከታታያችሁ ነኝ ከአማራ ክልል። ሁል ጊዜ መጠንቀቅ እና የጤና ባለሙያዎችን  ምክር መስማቱ ጥሩ ነው። ብለዋል።
»»»»»
አሁን ደግሞ የተወሰኑ በድምፅ የደረሱንን አስተያየቶች እናሰማችሁ
ድምፅ 
በመጨረሻም አንድ የአፋልጉኝ መልዕክት አለን
ደብዳቤ
እንግዲህ አድማጮች ለዛሬ ተራ የደረሳሳቸው መልዕክቶቻችሁ የስካሁኑ ነበሩ ። ፃፉልን ወይም ደውሉልን። መልዕክታችሁን ሳምንት ይዘን እንቀርባለን። መልካም በዓል እያልኩ ከወዲሁ የምሰናበታችሁ ልደት አበበ ነኝ። ጤና ይስጥልኝ።

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW