1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሱዳን፣ የመፈንቅለ መንግሥት ሐገር

ማክሰኞ፣ ኅዳር 7 2014

ኢትዮጵያ  ዉስጥ የተደረገዉ የለዉጥ ተስፋ ባጭር ተቀጭቶ፣ ሐገሪቱ በጦርነት  ስትወድም ሱዳንም ከአዲስ ፖለቲካዊ ቀዉስ መዘፈቋ ከሶማሊያና ከኤርትራ ነባር ቀዉስ ጋር ተዳምሮ ምስራቅ አፍሪቃን የግጭት፣የቀዉስና የአለመረጋጋትና ቀጠና አድርጎታል

Yesuf Yassien
ምስል privat

ቃለ መጠይቅ፣ «እናቱ ከረገመችዉ ጋር ከተጣመድክ፣ የእናትሕ ምርቃት ዋጋ የለዉም» አፋሮች

This browser does not support the audio element.


የሱዳን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥና የሽግግር ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ጄኔራል አብዱልፈታሕ አል ቡርሐን ባለፈዉ ጥቅምት አጋማሽ ከስልጣን ያስወገዷቸዉን ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሐምዶክና ካቢኒያቸዉን ወደ ስልጣን እንዲመልሱ ከዉጪም ከዉስጥም የሚደረግባቸዉን ግፊት አልተቀበሉትም።ጄኔራሉ ይባስ ብለዉ ባለፈዉ ሳምንት ሐሙስ አዲስ መንግስት መስርተዉ የመሪቱን ሥልጣን እንደያዙ ለመቀጠል ቃለ መሐላ ፈፅመዋል።
የሱዳን ሕዝብ እንደ ጎርጎሪያኑ አቆጣጠር ከ2018 ታሕሳስ ጀምሮ በተከታታይ ባደረገዉ የአደባባይ ሰልፍና ተቃዉሞ የሐገሪቱን የረጅም ጊዜ ገዢ ዑመር ሐሰን አልበሽርን ሚያዚያ 2019 ማስወገዱ ልክ እንደ ኢትዮጵያ ሁሉ ከሱዳን አልፎ ለምስራቅ አፍሪቃ ሠላም፣ዴሞክራሲና ልማት አዲስ ተስፋ ፈንጥቆ ነበር።
ይሁንና ኢትዮጵያ  ዉስጥ የተደረገዉ የለዉጥ ተስፋ ባጭር ተቀጭቶ፣ ሐገሪቱ በጦርነት  ስትወድም ሱዳንም ከአዲስ ፖለቲካዊ ቀዉስ መዘፈቋ ከሶማሊያና ከኤርትራ ነባር ቀዉስ ጋር ተዳምሮ ምስራቅ አፍሪቃን የግጭት፣የቀዉስና የአለመረጋጋትና ቀጠና አድርጎታል።የሱዳንን ፖለቲካዊ ቀዉስ መነሻ በማድረግ የፖለቲካ ተንታኝና ደራሲ የሱፍ ያሲንን ሥለ አካባቢዉ ፖለቲካዊ ቀዉስ አነጋግረናቸዋል።ሙሉ ቃለ ምልልሱን እነሆ

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW