1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ሱዳን የኢትዮጵያ ጦር «ወረራ ፈጽሞብኛል» ስትል ከሰሰች

ሰኞ፣ የካቲት 8 2013

ሱዳን የኢትዮጵያ ጦር ኃይል ድንበሬን ተሻግሮ «ወረራ ፈጽሞብኛል» ስትል ከሰሰች። የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ትናንት እሁድ እንዳስታወቀው ድርጊቱ በሁለቱ ሃገራት መካከል የነበረውን የድንበር ውዝግብ የሚያባብስ ነው ማለቱን ሮይተርስ ዘግቧል።

Äthiopien Sudan Grenzgebiet Landwirtschaft
ምስል፦ Alemnew Mekonnen/DW

ሱዳን የኢትዮጵያ ጦር ኃይል ድንበሬን ተሻግሮ «ወረራ ፈጽሞብኛል» ስትል ከሰሰች። የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ትናንት እሁድ እንዳስታወቀው ድርጊቱ በሁለቱ ሃገራት መካከል የነበረውን የድንበር ውዝግብ የሚያባብስ ነው ማለቱን ሮይተርስ ዘግቧል። ኢትዮጵያ የሱዳንን ድንበር ተሻግራ መግባቷ አሳዛኝ ነው ያለው መግለጫው ውጤቱ አደገኛ እና ተቀባይነት የሌለው እንዲሁም በቀጣናው ደህንነት እና መረጋጋት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል ብሏል። በኢትዮጵያ መንግሥት የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቃባይ በኩል በጉዳዩ ላይ ለጊዜው የተሰጠ ምላሽ ባይኖርም ቀደም ሲል የሱዳን ጦር የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ መግባቱን አስታውቆ ነበር። የአሁኑ የሱዳን ክስ ከመሰማቱ በፊት  የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለፈው ቅዳሜ በፌስ ቡክ ገጹ እንዳስታወቀው ሱዳን ውስጥ ከጥቅምት ወር የመጨረሻ ቀናት ጀምሮ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጸሙ ዝርፍያ እና የማፈናቀል ተግባራት እንዲቆም አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለሱዳን መንግሥት ጥሪ ማቅረባቸውን ገልጿል። አምባሳደር ዲና  አያይዘው «ኢትዮጵያ የሁለቱን ሃገራት የድንበር ይገባኛል ጥያቄን በሦስተኛ ወገን መሸማገል አትፈልግም፤ የሱዳን ጦር በኃይል የተቆጣጠራቸውን አካባቢዎች ለቆ መውጣት ይኖርበታል ።» ማለታቸውም ተዘግቧል። ሱዳን ባለፈው ወር « የኢትዮጵያ የጦር አውሮፕላን ድንበሬን ተሻግሮ ገብቷል » ስትል የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ድርጊቱን አስተባብሎ ነበር። እንደሮይተርስ ዘገባ በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ባለው የለም መሬት ላይ በሁለቱ ሃገራት መካከል የተፈጠረው የድንበር ይገባኛል ጥያቄ አንድ ክፍለ ዘመን ተሻግሯል።

 

ታምራት ዲንሳ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW