ሱዳን ድንበሮቿን መዝጋቷ
ቅዳሜ፣ ጥቅምት 28 2013
ማስታወቂያ
ኢትዮጵያውያንና ሱዳናውያንን ከሚያገናኙ ኬላዎች መካከል አንዱ የመተማ ገላባት ኬላ ነው፡፡ መተማና ገላባት ከተሞች የሚለያዩት 30 ሜትር በሚረዝም አንድ ድልድይ ነው፤ አንዱ ወደሌለኛው በመሻገር ከፍተኛ የንግድ ልውውጥ ያደርጋሉ፣ ሱዳንንና ኢትዮጵያን በየብስ የሚያገናኘው አቢይ መንገድም በዚሁ አቅጣጫ ይገኛል፡፡ ኬላው በተለያዩ ምክንያቶች አንዴ ይዘጋል፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ይከፈታል፣ በቅርቡ ከኮቪድ ጋር በተገናኜ በፌደራል መንግስት ኬላው ተዘግቶ አንደነበር ነዋሪዎች ይናገራሉ፣ ለጥቂት ቀናት አገልግሎት መስጠት ቢጀምርም ሰሞኑን ደግሞ ከኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ አገልግሎቱን አቋርጧ፡፡ አንድ የመተማ ዮሐንስ ከተማ ነዋሪ ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት ኬላው ቀደም ሲል በኮቪድ ምክንያት ተዘግቶ የቆየ ቢሆንም ለትቂት ቀናት ከተከፈተ በኋላ ሰሞኑን ከተፈጠረው አገራዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ እንደገና ተዘግቷል፡፡ ሱዳን ከወቅቱ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ሁኔታ ጋር በተገናኘ የሚያጎራብታትን የድንበር አካባቢ መዝጋቷን የሀገሪቱ የዜና ምንጮች ይፋ አድርገዋል። ከባሕር ዳር ዘጋቢያችን ዓለምነው መኮንን ዘገባ አለው።
ዓለምነው መኮንን
ሸዋዬ ለገሠ