1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቁጥሩ የማይታወቅ ሰዉ ሞተ

ዓርብ፣ ሐምሌ 12 2011

መኪኖች፤ መኖሪያና መስሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል። መደብሮች ተመዝብረዋልም። የተለያዩ ከተሞችን የሚያገናኙ የመኪና መንገዶች ሲዘጉ፤ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት በከፊል ተቋርጧል።

Äthiopien Stadtansicht Awassa
ምስል DW/S. Wegayehu

የሲዳማ ዞን ግጭትና ሁከት

This browser does not support the audio element.

የሲዳማ ዞን በክልል እንዲደራጅ የቀረበዉ ጥያቄ አፋጣኝ አወንታዊ መልስ እንዲሰጠዉ ግፊት የሚያደርጉ የሲዳማ ፖለቲከኞች በተለይ ወጣቶች በየከተማዉ ከሰፈረዉ የፀጥታ አስከባሪ ጋር እየተጋጩ ነዉ። ነዋሪዎች እንደገለፁት በግጭትና ሁከቱ ቁጥራቸዉ በዉል ያልታወቁ ሰዎች ተገድለዋል።መኪኖች፤ መኖሪያና መስሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል። መደብሮች ተመዝብረዋልም። የተለያዩ ከተሞችን የሚያገናኙ የመኪና መንገዶች ሲዘጉ፤ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት በከፊል ተቋርጧል። ሐዋሳ ዉስጥ ትናንት በፀጥታ አስከባሪዎችና በወጣቶች መካከል በተፈጠረዉ ግጭት ቢያንስ አንድ ሰዉ ተገድሎ፣ ሌሎች ሦስት ቆስለዋል። ወኪላችን ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ እንደዘገበዉ ሐዋሳ ዛሬ ተረጋግታለች።

ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW