1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ሳልሳይ ወያኔ «ሕገ መንግሥት ለማሻሻል እታገላለሁ»

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 29 2012

የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ላይ ማሻሻያ ለማድረግ እንደሚታገል ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ዐስታወቀ። በቅርቡ በትግራይ ከተመሰረቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል አንዱ የሆነው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት) አመራሩን መርጦ ፕሮግራሙንም ያጸደቀው ባለፈው ቅዳሜ እና እሁድ ባደረገው የመጀመሪያ ድርጅታዊ ጉባኤው ነው።

Äthiopien Pressekonferenz der TPLF mit Salsay Weyane
ምስል፦ DW/M. Hailesilassie

ለትግራይ ሕዝብ እታገላለሁ ብሏል

This browser does not support the audio element.

የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ላይ ማሻሻያ ለማድረግ እንደሚታገል ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ዐስታወቀ። በቅርቡ በትግራይ ከተመሰረቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል አንዱ የሆነው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት) አመራሩን መርጦ ፕሮግራሙንም ያጸደቀው ባለፈው ቅዳሜ እና እሁድ ባደረገው የመጀመሪያ ድርጅታዊ ጉባኤው ነው። የሳልሳይ ወያነ ትግራይ ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት አቶ ኃያሉ ጎደፋይ ድርጅታቸው የትግራይን ጥቅም መሰረት ያደረገ ትግል እንደሚያደርግም  መቀሌ  ባሎኒ ሆቴል  ውስጥ ሰኞ ማታ በሰጡት መግለጫ ገልጠዋል።  ከዚህ በተጨማሪም ሳልሳይ ወያነ ትግራይ የኢትዮጵያ ሕገ- መንግሥት ጠንካራ ክልሎችን በሚፈጥር ሁኔታ እንዲሻሻል ለማድረግ እንደሚታገል ሊቀ መንበሩ ተናግረዋል፡፡ ዝርዝሩን ሚሊዮን ኃይለሥላሴ ከመቀሌ ልኮልናል። 

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ  

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW