1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሳልሳይ ወያኔ ትግራይ ዉስጥ መንቀሳቀስ አልቻልኩም አለ

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 25 2014

በትግራይ ክልል የፖለቲካ ምህዳሩ «ሙሉ በሙሉ» ተዘግቷል ያለው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ የተባለው ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት በክልሉ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ መቸገሩን ገለጸ። ፖርቲው በሰጠው መግለጫ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ቅዳሜ በመቐለ የጠራው ሕዝባዊ ስብሰባ በታጣቂ ኃይሎች መበተኑን ዐስታውቋል።

Tigray | Logo | Salsay Weyane Tigray
ምስል Salsay Weyane Tigray

«መቐለ እስከ 600 ሰዎች በታጣቂ ኃይሎች ተበትነዋል»

This browser does not support the audio element.

በትግራይ ክልል የፖለቲካ ምህዳሩ «ሙሉ በሙሉ» ተዘግቷል ያለው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ የተባለው ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት በክልሉ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ መቸገሩን ገለጸ። ፖርቲው በሰጠው መግለጫ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ቅዳሜ በመቐለ የጠራው ሕዝባዊ ስብሰባ በታጣቂ ኃይሎች መበተኑን ዐስታውቋል። በተለይም በትግራይ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም የጠሩ የፖለቲካ ፖርቲዎች ተለይተው ዓፈና እየደረሰባቸው መሆኑን የሚገልፀው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ኹኔታውን ሕገ ወጥና ፀረ ዴሞክራሲ ብሎታል።

ከዚህ በተጨማሪ ፖርቲው ትግራይ ክልል በአስከፊ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ላይ እንደምትገኝ ገልጿል። ለዚህም ተጠያቂዎች ያላቸውን አካላት ጠቅሷል። ለችግሩ ተጠያቂዎች ትግራይ ክልል ላይ «መዘጋትና ከበባ» የጣለው የኢትዮጵያ መንግስት እንዲሁም «ሁኔታውን መምራት ያልቻለው» በሕወሓት የሚመራው የትግራይ ክልል አስተዳደር ናቸው ብሏል።

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW