የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነት
ረቡዕ፣ ሰኔ 20 2010ማስታወቂያ
የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳላቫ ኪር እና የአማጽያኑ መሪ ሪየክ ማቻር ዛሬ ካርቱም ውስጥ የሰላም ስምምነት ተፈራረሙ። ሁለት ወገኖች ካርቱም ሱዳን ውስጥ ለሁለት ቀናት ካካሄዱት ድርድር በኋላ የተፈራረሙት ስምምነት ተኩስ አቁምን ያካትታል። የሰላም ስምምነቱ ዓላማም በአስር ሺህዎች የሚቆጠር ህዝብ ህይወት የጠፋበትን ጦርነት ማስቆም መሆኑ ተገልጿል። ሁለቱ ወገኖች ተኩስ አቁም ተግባራዊ በሚሆንበት መንገድ እና ስለ ሥልጣን ክፍፍል እዚያው ካርቱም ውስጥ መወያየት እንደሚቀጥሉ የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አል ዲርዲሪ ሞሀመድ አህመድን ጠቅሶ ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል። የአማጽያኑ መሪ ማቻር ለሥልጣን ክፍፍል እንዲያመች ለደቡብ ሱዳን ሦስት ዋና ከተማ እንዲኖር የቀረበውን ሃሳብ መቃወማቸው ተዘግቧል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ