1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሳዑዲ፥ የኢትዮጵያዉን ቅሬታ እና የቆስሉ መልስ

ረቡዕ፣ ግንቦት 21 2005

ኢትዮጵያዉያኑ ለታላቁ ምሕረት ታላቅ ዕድለኛ ለመሆን፥ የታደሰ፥ ወይም አዲስ የወጣ ፓስፖርት መያዝ፥ ወኪል ወይም ስፖንሰር ማግኘት ግድ ከሚሆኑባቸዉ ቅድመ-ሁኔታዎች ዋና፥ ግን ጥቂቶቹ ናቸዉ።ጊዜዉ ግን አጭር ነዉ።አንድ ወር።

Achtung: schlechte Qualität. Auf Wunsch von Ludger Schadomsky trotzdem eingestellt. Nebiyu Sirak/DW Titel: Äthiopische Flüchtlinge in Saudi Thema: Mehrere tausend äthiopische Flüchtlinge warten in schlechten Verhältnissen in Abschiebeurterkünften in Saudi Arabien auf Ihre Deportierung nach Äthiopien. Stichworte: Äthiopien, Flüchtlinge, Saudi Arabien, UNHCR, Flüchtlingskonvention
ኢትዮጵያዉን ስደተኞች-ጂዳሕምስል Nebiyu Sirak

የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ያለ ሕጋዊ ፍቃድ በሐገሩ የሚኖሩ የዉጪ ሐገር ዜጎች ሕጋዊ ፍቃድ እንዲያገኙ ያደረገዉ ምሕረት እዚያ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን እና በጂዳሕ ለኢትዮጵያ ቆስላ አዲስ የዉዝግብ ሰበብ ሆኗል።ጂዳሕና በአካባቢዉ የሚኖሩ የኢትዮጵያዉን ቆስላዉ በተገቢዉ ጊዜ ፓስፖርታችንን ባለማደሱ ወይም አዲስ ፓስፖርት ባለመስጠቱ የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት በደነገገዉ የምሕርት ቀነ-ገደብ እንዳንጠቀም እያደናቀፈን ይላሉ።የቆስላዉ ሐላፊ ግን የነዋሪዎችን ጥያቄ ለማሟላት ቀን-ከሌት እየሠራን ነዉ ባይ ናቸዉ።ነጋሽ መሐመድ ባለጉዳዮችችን አነጋግሮ ያጠናቀረዉ ዘገባ አለዉ።

የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ያወጀዉ ምሕረት ብዙዎች እንደሚያምኑት በአስር ሺሕ ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉን ስደተኞች ምናልባት እድሜ-ልክ የማይገኝ አይነት ነዉ።በሕገ-ወጥነት እየተሸማቀቁ ከመኖር፥ የክፉ ቀጠሪዎችን፥ የጨካኝ አቀባባይ ደላሎችን፥ ግፍ፥ በደል «አሜን» ብሎ ከመቀበል የሚገላግል፥ሕጋዊነትን የሚያጎናፅፍ ታላቅ ዕድል።

ኢትዮጵያዉያኑ ለታላቁ ምሕረት ታላቅ ዕድለኛ ለመሆን፥ የታደሰ፥ ወይም አዲስ የወጣ ፓስፖርት መያዝ፥ ወኪል ወይም ስፖንሰር ማግኘት ግድ ከሚሆኑባቸዉ ቅድመ-ሁኔታዎች ዋና፥ ግን ጥቂቶቹ ናቸዉ።ጊዜዉ ግን አጭር ነዉ።አንድ ወር።

አዋጁ እንደሰተሰማ ሐበሻ-ይጣደፍ ገባ።ከመጀመሪያዉ-መጀመር አለበት።ፓስፖርት።ሩጫ ወደ ኢትዮጵያ ቆንስላ።ጂዳሕ።

በጂዳሕ የኢትዮጵያ ቆስላ ጄኔራል አቶ ዘነበ ከበደ ወቀሳ ትችቱን አይቀበሉትም።---የአቶ ዘነበ ማብራሪያ ለነዋሪዎቹ አሳማኝ አይደለም።----
እንደገና ኮንሱል ጄኔራል ዘነበ።

ጊዜም ማንንም አይጠብቅም።

ምስል AP
ምስል DW

ነጋሽ መሐመድ

ሂሩት መለሠ




ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW