1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስለተራዘመው የሕዝብ ቆጠራ የአብን መግለጫ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 10 2011

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) 4ኛው የህዝብና ቤቶች ቆጠራ መራዘሙ ተገቢ ቢሆንም፤ በ3ኛው ህዝብና ቤቶች ቆጠራ የተሳተፉ አመራሮች እንዲጠየቁ፣ መንግስት ይቅርታ እንዲጠይቅ፣ ውጤቱም በይፋ እንዲሰረዝ እና ካሳ ለሚገባቸው እንዲከፈል ጠየቀ።

Äthiopien PK National movement of Amhara in Addis Abeba
ምስል DW/S. Mushie

የአብን መግለጫ

This browser does not support the audio element.

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) 4ኛው የህዝብና ቤቶች ቆጠራ መራዘሙ ተገቢ ቢሆንም፤ በ3ኛው ህዝብና ቤቶች ቆጠራ የተሳተፉ አመራሮች እንዲጠየቁ፣ መንግስት ይቅርታ እንዲጠይቅ፣ ውጤቱም በይፋ እንዲሰረዝ እና ካሳ ለሚገባቸው እንዲከፈል ጠየቀ። ፓርቲው በ3ኛው የህዝብ እና ቤቶች ቆጠራ ወቅት በአማራ ፣ በአዲስ አበባ ፣ በጉራጌ እና በቅማንት ህዝቦች ላይ ፖለቲካዊ የሆነ ህዝብን ያለመቁጥር  የተቆጠረውንም ያለማሳወቅ ወንጀል ተሰርቷል ብሏል። በመሆኑም የህግ ማዕቀፉና መዋቅሩ ተስተካክሎ ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለበት አሰራር መስፈኑ ሲረጋገጥና አገሪቱ ያለችበት ወቅታዊ የመፈናቀል ችግር ሲቀረፍ ብቻ አሁን የተራዘመው የህዝብና ቤቶች ቆጠራ ሊከናወን ይገባል ሲል ዛሬ በሰጠው መግለጫ አመልክቷል። ለዝርዝሩ ሰለሞን ሙጬ ከአዲስ አበባ።
ሰለሞን ሙጬ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW