1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ስለአባይ ግድብ ኢትዮጵያ ለተባበሩት መንግሥታት ጥሪ ማቅረቧ

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 12 2013

በመጪው ክረምት የ«ታላቁ የሕዳሴ ግድብ»ን ሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሌት እንደምታከናውን ያሳወቀችው ኢትዮጵያ፦ ለተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ደብዳቤ አስገብታለች። በደብዳቤውም ድርድሩ በአፍሪቃ ሕብረት እንዳይቋጭ እንቅፋት ሆነዋል ያለቻቸው የተፋሰሱ ሀገራት ላይ ተመድ ጫና እንዲያደርግ መጠየቋ ተገልጧል።

Äthiopien Grand-Ethiopian-Renaissance-Talsperre
ምስል፦ AFP/Maxar Tech

ኢትዮጵያ ተመድ ጫና እንዲያደርግ ጠይቃለች

This browser does not support the audio element.

በመጪው ክረምት የ«ታላቁ የሕዳሴ ግድብ»ን ሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሌት እንደምታከናውን ያሳወቀችው ኢትዮጵያ፦ ለተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ደብዳቤ አስገብታለች። በደብዳቤውም ድርድሩ በአፍሪቃ ሕብረት እንዳይቋጭ እንቅፋት ሆነዋል ያለቻቸው የተፋሰሱ ሀገራት ላይ ተመድ ጫና እንዲያደርግ መጠየቋ ተገልጧል። ግብፅና ሱዳን የግድቡ ጉዳይ ከአፍሪቃ ኅብረት በተጨማሪ በሌሎች አካላትም እንዲታይ በመጠየቅ ኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲደረግ ግብጽ ለተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት አቤት ማለቷ ይታወሳል። ኢትዮጵያ ለተመድ ደብዳቤ ማስገባቷ በዓለም አቀፍ ሕግ መሰረት አገራት ጉዳዩ የሰላምና ፀጥታ መናጋት ይፈጥራል ብለው ሲያስቡ የሚያደርጉት መሆኑን ባለሞያዎች ይናገራሉ።

ሰለሞን ሙጬ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

እሸቴ በቀለ
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW