1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስለኢትዮጵያ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት የጥናት ውጤት

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 19 2014

ኢትዮጵያ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት አላቸው ከሚባሉ ዐሥር የአለም ሀገራት ዘጠነኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማኅበር ጥናት አመለከተ። ማኅበሩ በኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት ፣ በዋጋ ግሽበት እና ችግሮች ዙሪያ ለስድስት ወራት ያደረገውን ጥናት ዛሬ ይፋ ሲያደርግ እንዳለው የዋጋ ግሽበት የኢትዮጵያ የወቅቱ አንገብጋቢ ጉዳይ ሆኗል ብሏል።

Äthiopien | Ethiopian Economic Association Pressekonferenz
ምስል Solomon Muchie/DW

«የዋጋ ግሽበት የኢትዮጵያ አንገብጋቢ ጉዳይ ሆኗል»

This browser does not support the audio element.

ኢትዮጵያ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት አላቸው ከሚባሉ ዐሥር የአለም ሀገራት ዘጠነኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማኅበር ጥናት አመለከተ። ማኅበሩ በኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት ፣ በዋጋ ግሽበት እና ችግሮች ዙሪያ ለስድስት ወራት ያደረገውን ጥናት ዛሬ ይፋ ሲያደርግ እንዳለው የዋጋ ግሽበት የኢትዮጵያ የወቅቱ አንገብጋቢ ጉዳይ ሆኗል ብሏል። የተፈጠረው የኑሮ ውድነት የኅብረተሰቡን ኅልውና እየተፈታተነ ይገኛል ሲልም አክሏል።  ጥናቱ በጥራጥሬ እህል፣ በአትክልት እና ፍራፍሬ፣ በሥጋ እና ወተት ተዋጽዖ ምርቶች ላይ ከፍተኛ የአቅርቦት ማሽቆልቆል እንደተከሰተ ዐሳይቷል። የኢንዱስትሪ ምርትና የአገልግሎት ዘርፍ ማደግ የዋጋ ግሽበትን አባባሽ ሆኖ መገኘቱም ተገልጿል። ከውጭ የሚገቡ የምግብ፣ የነዳጅ እና የማዳበሪያ ሸቀጦች በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ምክንያት የዋጋ ግሽበቱን ማባባሳቸውም ተገልጿል። 

ከምግብ ፍጆታዎች ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት የታየባቸው የግብርና ምርቶች እህል ፣ የቁም እንስሳት ተዋጽዖ፣ ቀጥታ ለምግብ ከሚውሉት ዳቦ እና አትክልት እና ፍራፍሬ ይገኙበታል ብሏል ጥናቱ።  ምግብ ነክ ካልሆኑት የዋጋ ንረት አባባሽ ጉዳዮች መካከል ደግሞ የቤት ክራይ ፣ የውኃ እና የመብራት፣ የህክምና እንዲሁም የትራንስፖርት ዋጋዎች ዋና ዋናዎቹ ናቸው። 

ማኅበሩ በአጭር ጊዜ ብሎ ካስቀመጣቸው የመፍትሔ አማራጮች መካከል የመጀመርያው የአቅርቦትና የዋጋ ማረጋጊያ ሥርዓትን የሚመራ ተቋም እንዲቋቋም የጠየቀበት ነው።  ፍራንኮ ቫሎታ ወይም የውጭ ምንዛሪ ያላቸው ዜጎች በተመረጡ ሸቀጦች በተለይ ለመድሃኒት ፣ ለግንባታ እቃዎች፣ ለመሰረታዊ የምግብ ሸቀጦች፣ የግብርና እና የቴክኖሎጂ ምርቶች ላይ ተፈቅዶ እንዲሠራ አመልክቷል። በሌላ በኩል የተቀማጭ ወለድ እንዲጨምር እና የማበደሪያ ወለድ እንዲቀንስ ማድረግ አማራጭ ሆኖ ቀርቧል። መንግሥት የአገር ውስጥ ያለውን ግጭት መፍታት እና ሰላም እንዲሰፍን ማድረግም ዋነኛ የመፍትሔ ሀሳቦች ሆነው ተቀምጠዋል።

ሰለሞን ሙጬ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW