1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስለኮሮና ተሐዋሲ የህክምና ባለሙያዎች ምን ይላሉ?

ማክሰኞ፣ መጋቢት 15 2012

በዛሬው ዕለት ይፋ በሆነ መረጃ መሠረት በመላው ዓለም በኮቪድ 19 ማለትም በኮሮና ተሐዋሲ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 396,236 ደርሰዋል። ከህመሙ ያገገሙት ከ103 ሺህ አለፍ ብለዋል። በተሐዋሲው  በመላው ዓለም ሕይወታቸውን ያጡት ደግሞ 17,250 መሆናቸው ተመዝግቧል።

Deutschland Erste Todesfälle nach Infektionen mit Coronavirus | Symbolbild Test
ምስል Imago-Images/photothek/T. Trutschel

ስለኮሮና ተሐዋሲ የህክምና ባለሙያዎች ምን ይላሉ?

This browser does not support the audio element.

ኮቪድ 19 ማለትም ኮሮና ተሐዋሲ መጀመሪያ በአንድ ሰው ላይ ከታየ በኋላ 100 ሺህ ሰዎችን ለመልከፍ 67 ቀናት እንደወሰደበት፤ ሁለት መቶ ሺህ ለመሙላት ግን ተጨማሪ 11 ቀናት ብቻ እንዳስቆጠረ የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ተናግረዋል። በተሐዋሲው የተያዙ ሰዎች 300 መሙላታቸው በተሰማ ከሁለት ቀናት በኋላ ዛሬ ደግሞ አጠቃላይ ቁጥራቸው 396,236 መድረሱ ይፋ ሆኗል። ኮሮና ተሐዋሲ ባለው  የመጋባት ፍጥነት የሚለክፈው ሰው እየጨመረ ስለሚሄድም ምናልባት በቅርቡ በየሃገራቱ የታማሚው ቁጥር 100 ሺህ  ሊሞላ እንደሚችል የዓለም የጤና ድርጅት ግምቱን አመላክቷል። ዓለምን አስጨንቆ ያደናገጠው አዲሱ ተሐዋሲ የፍጥነቱን ያህል ተገቢው ጥንቃቄ በተወሰደባቸው እንደቻይና እና ጃፓን ያሉ ሃገራት የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መቀነስ ብቻ ሳይሆን የወትሮው ሕይወት እያንሰራራ መሆኑ ደግሞ በሌላ በኩል እየተሰማ ነው። ፕሮፌሰር ያሬድ ወንድምኩን በዩናይትድ ስቴትሷ ቨርጂኒያ ግዛት የውስጥ ደዌ ህክምና ባለሙያ ናቸው።  ሙሉ ቅንብሩን ከድምፅ ማዕቀፉ ያድምጡ።

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW