1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስለጤናዎ በማኅበራዊው መገናኛ ዘዴ

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 12 2017

ማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የተለያዩ ተግባራት ይከናወኑባቸዋል። ዛሬ የዕድሜ እና ጾታ ልዩነት ሳይኖረው ይህን የመረጃ ምንጭና የሃሳብ መለዋወጫ መድረክ በርካቶች ይጠቀሙበታል። የህክምና ባለሙያዎችም የተለያዩ ጤናነክ መረጃዎችን እያቀረቡበት ነው።

ዩ ትዩብ
ዩትዩብና ሌሎች የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴ መድረኮችን በመጠቀም ጥቂት የማይባሉ የሕክምና ባለሙያዎች ለኅብረሰተቡ ስለጤናው ግንዛቤ ለመስጠት ጥረት እያደረጉ ነው። ፎቶ ከማኅደርምስል picture-alliance/dpa/M. Skolimowska

ስለጤናዎ በማኅበራዊው መገናኛ ዘዴ

This browser does not support the audio element.

 

በኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ከህክምና ዶክተሮች አኳያ ሲሰላ

የዓለም ባንክ በጎርጎሪዮሳዊው 2020 ዓ,ም ያወጣው አንድ የኤኮኖሚ ይዞታ ማሳያ መዘርዝር ኢትዮጵያ ውስጥ ለአንድ ሺህ ታማሚዎች አንድ ዶክተር፣ ለአንድ ሺህ ወላዶች ደግሞ አንድ ነርስ ወይም አዋላጅ ብቻ መኖራቸውን ያሳያል። በሀኪም ቤት ደረጃ ደግሞ፤ አንድ የሀኪም ቤት መኝታ አልጋ ለአንድ ሺህ ታካሚዎች መሆኑን፤ የቀዶ ህክምና የሚያደርጉ ከፍተኛ የህክምና ባለሙያዎች ደግሞ አንዱ ለመቶ ሺህ ሰው እንደሆነ ይዘረዝራል። የህክምናውን ሁኔታ እና የታካሚዎችን ልማድ ያስተዋሉ አንዳንድ የህክምና ባለሙያዎች ታዲያ በዘመናችን ኅብረተሰቡ በቀላሉ ይገኝበታል በሚባው የማኅበራዊ መገናኛ መድረክ ጠቃሚ የህክምና መረጃዎችን ለማጋራት ጥረት እያደረጉ ነው።

ዶክተር ሰይፈ ወርቁ፤ ስለጨጓራ በሽታ፤ ስለሆድ ድርቀት፤ ስለነርቭ በሽታ፤ ስለደም ማነስ፤ ስለጉልበት ህመም፤ ስለተረከዝ ህመም ፤ ስለተለያዩ የቆዳ ችግሮች፤ ስለፀጉር ጤናና ክብካቤ እንዲሁም ስለተለያዩ ቫይታሚኖች አጠቃቀም፤ እያሉ ስለተለያዩ የውስጥና የቆዳ ህመሞችና በርካታ ጤናን የሚመለከቱ መረጃ እና ማብራሪያዎችን፤ ከጠቃሚ የመፍትሄ ምክሮች ጋር በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አቅርበዋል፤ በየጊዜውም ያቀርባሉ። አድማጮቻቸውም በርካቶች ናቸው።

ምን ያህሉ የኅብረተሰብ ክፍል ሙያዊ ምክሩን በተግባር ተጠቅሞበት ይሆን?

ከዕለታዊ ሥራቸው በተጓዳኝ እንዲህ ያለውን የበጎ ፈቃድ ማኅበራዊ አገልግሎት ለመስጠት ያነሳሳቸው ምክንያት ብዙ ነው የሚሉት ዶክተር ሰይፈ በተለይ በርካታ ሀኪሞች የሚያነሱት ወሳኝ ችግር እንደገፋፋቸው ይናገራሉ። እንዲያም ሆኖ ምን ያህሉ አድማጫቸው በሚደረጉ ጤናነክ ገለጻና ማብራሪያዎች እንዲሁም ምክሮች እየተጠቀሙ ይሆን የሚለው መሠረታዊ ጥያቄ ይሆናል። እንዲህ ያለውን ጠቃሚ የህክምና መረጃ እና ማብራሪያ የሚስተላልፉት ዶክተር ሰይፈ ግን ምንም እንኳን በርካቶች እንደሚያደምጧቸው፤ አስተያየትም እንደሚሰጧቸው ቢገልጹም፤ ስንቶቹ በተግባር እየተጠቀሙበት ነው ለሚለው ያንን የሚገልጽን ለመመዘን እንዳልሞከሩ ተናግረዋል።

በነገራችን ላይ ዶክተር ሰይፈም እንደጠቆሙት ለጤና በሚል ያልተጣሩና ያልተረጋገጡ፤ መረጃዎችን በዘፈቀደና በድርፍረት የሚያስተላልፉም ጥቂት አይደሉም። ትክክለኛ የህክምና መረጃዎችን መርጦ ለመውሰድ የማኅበራዊ መገናኛው ተጠቃሚዎችን ማስተዋልና ጥንቃቄ ይጠይቃል። አድማጮች፤ በማኅበራዊ መገናኛ ኅብረተሰቡ ስለጤና ግንዛቤ እንዲኖረው ጥረት የሚያደርጉት ዶክተር ሰይፈ ወርቁን ለጊዜያቸው እናመሰግናለን።

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW